ለሀገራዊ ማንነትና እሴት ግንባታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ   የምክክር መድረክ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ፡፡

ለሀገራዊ ማንነትና እሴት ግንባታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ፡፡

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ”ለሀገራዊ ማንነትና እሴት ግንባታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና ” በሚል ርዕስ ያዘጋጀው፣ ወልዲያ፣ ወሎ እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ተጋባዥ የሆኑበት የምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡

የእለቱ የክብር እንግዳ የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስተር ዲኤታ የተከበሩ አቶ ታየ ደንደኣ በንግግራቸው እንዳገለፁት ሰመራ ዩኒቨርሲቲ አራት ዩኒቨርሲቲዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማሰባሰብ ይህን የመሰለ መድረክ በማዘጋጀቱ እንደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለሀገር ግንባታ አስተዋፅኦው ከፍተኛ ነው ፣ እንደ ሰላም ሚኒስቴርም፣ ሀብትን ፣ ጊዜን ማጥፋት ካለብን ለሰላም እና የጋራ ሀገር ግንባታ መሆን አለበት ብለን እናምናለን ሲሉ አብራርተዋል።

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲያችን ከመማር ማስተማር ስራችን ባለፈ ለሀገር ግንባታ እና አብሮነት  የበኩላችንን አስተዋፅዖ ለማበርከት በማሰብ ሶስቱን ጎረቤት ዩኒቨርሲቲዎች በመጋበዝ ያዘጋጀው መድረክ በመሆኑ ለጋራ ሀገራችን የየራሳችን ሀሳብ ማዋጣት ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአንትሮፖሎጂ መምህር እና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ የውይይት መነሻ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበው: ከቤቱ ሀሳብ እና አስተያየቶች ከተሰጠ በሗላ:አቶ ታየ ደንደአ የሚመሩት የየዩኒቨርሲቲወቹ ፕሬዚዳንቶች ተወካዮች ውይይት አድርገዋል::

በመድረኩ የተከበሩ አቶ ታየ ደንደኣ የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስተር ዲኤታ ፣ የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አበበ ግርማ፣ የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕ/ር ታደሰ ደጀኔ፣ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች፣ እንዲሁም የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እና መምህራን ተሳትፈውበታል።

በፕሮግራሙ ማጠቃለያ አራቱ ዩኒቨርሲቲዎች በቀጣይ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችን በማቀፍ ስለ ሀገር ግንባታ የሚወያዩበት እና የበኩላቸውን አስተዋፅዖ የሚያበረክቱበት “ዳሎል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም  ለሀገር ግንባታ” Dalol Forum of Ethiopian Higher learning Institutions for Nation Building  ( DFN) መስርተዋል።

==============

የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.