ለ20ኛው አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው በህብረት እንታገል” በሚል መሪ ቃል በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ፡፡

ለ20ኛው አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው በህብረት እንታገል” በሚል መሪ ቃል በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ፡፡

ለ20ኛው አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው በህብረት እንታገል” በሚል መሪ ቃል በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ፡፡
============
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ:- ህዳር 18: 2016 ዓ.ም

ለ20ኛ ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ እየተከበረ የሚገኘውን አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው በህብረት እንታገል” በሚል መሪ ቃል በሰመር ዩኒቨርሲቲ ተከብሯል፡፡

መድረኩን የከፈቱት የአስተዳደር ጉዳዮች ም/ ፕሬዚዳንት እና ወ / ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሁሴን ኡመር “ሙስና በገንዘብ ብቻ የሚገለፅ ሳይሆን ጊዜን ፣ ጉልበትን ፣ ሀሣብን እንዲሁም ሀላፊነትን በአግባቡ አለመወጣት ሁሉ እንደ ሙስና ይገለፃል ” ሲሉ ተናግረዋል።

በአለም እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የፀረ-ሙስና ስራዎች፣ እየተወሰዱ የሚገኙ እርምጃዎችን ፣ የሀብት ምዝገባን እና ሙስናን በጋራ በመከላከሉ ረገድ የባለድርሻ አካላት አስተዋፅዖ የተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፅሁፍ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ስራ-አስፈፃሚ አቶ ሁሴን ከበደ አቅርበዋል።

የሰራተኞች ሀብት ምዝገበ‍ የማስጀመሪያ ንቅናቄ እና ገለጻ በመድረኩ ተከናዉኗል።

መድረኩን ያዘጋጀው የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና መከታተያ ስራ አስፈፃሚ ሲሆን፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተሳታፊ ሆነዋል።
===========
ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!
የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ

Leave a Reply

Your email address will not be published.