ሰመራ  ዩኒቨርሲቲ፣ Pelum Ethiopia Consortium እና ገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ የሶስትዮሽ የመግበባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ Pelum Ethiopia Consortium እና ገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ የሶስትዮሽ የመግበባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ Pelum Ethiopia Consortium እና ገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ የሶስትዮሽ የመግበባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
====================================
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፡ ህዳር 07/2015 እ.ኢት.አ

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ Pelume Ethiopia Consortium እና የገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የሶስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ፊርማውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን የPelum Ethiopia Consortium ዳይሬክተር ዶ/ር ሃይላይ እና የገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ ዲን አቶ መሀመድ ሀመዱ በዩኒቨርሲቲው በመገኘት ተፈራርመዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን ስራችን የሚለካው በመፈራረም ሳይሆን መሬት አውርደን ሰርተን ለማህበረሰቡ በምናመጣው ጥቅም በመሆኑ ይህንን ታሳቢ አድርገን እንሰራለን ሲሉ ዩኒቨርሲቲው ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የተሰጡትን የመማር ማስተማር፣ የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች በያዛቸው የግብርና፣ የቱሪዝም እና የማእድን የልህቀት መስክ መሰረት ከተቋማቱ ጋር ውጤት ያለው ስራ መስራት እንደሚፈልግ ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡

ስምምነቱ ዩኒቨርሲቲው ሊከፍተው ላሰበው የብዝሃ ህይወት ማእከል በዘርፉ በተለይም በክልሉ በተለያዩ ወረዳዎች ሰርቶ የሚያውቀው Pelum Ethiopia Consortium በስልጠና እና ታላላቅ ድርጅቶችን በማገናኘት በኩል ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው የፊርማው አስተባባሪ ዶ/ር መሀመድ ሹምባህሪ አብራርተዋል፡፡

የPelum Ethiopia Consortium ዳይሬክተር ዶ/ር ሃይላይ በበኩላቸው ስምምነቱን መፈራረማቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀው ተቋማቸው በክልሉ በሳሙረቢ እና በኩነባ ወረዳዎች የሰራውን ስራ እንደ ጥሩ ልምድ በመጠቀም ከተቋሞቹ ጋር ሰፊ ስራ እንደሚሰሩ አብራርተዋል፡፡

የገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ ዲን አቶ መሀመድ ሀመዱ ተጠሪነቱ ለሙያና ክህሎት ሚኒስተር የሆነው የገዋኔ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ በእንስሳት እርባታ፣ በአትክልት እና ፍራፍሬ እና በሌሎች ዘርፎች የአካባቢውን ወጣቶች በማደራጀት ፍሬያማ ስራ ሊሰራ እንደሚችል በፊርማው ስነ ስርአት ላይ ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም ኮሌጁ ለፊርማው ካሳየው ፍጥነት በላይ ስራውን በተግባር ለማሳየት እና የሚጠበቀው ውጤት እንድመጣ ለማስቻል ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
============================
Facebook 👇
https://www.facebook.com/susamara2008/
Telegram 👇 https://t.me/SamaraUniversityEthiopia
You tube 👇 https://youtube.com/channel/UCvDWGawVYKQa_FJY8supkBA?sub_confirmation=1
የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!

Facebook (https://www.facebook.com/susamara2008/)
Samara University, Samara, Ethiopia
Samara University, Samara, Ethiopia, Logya, Welo, Ethiopia. 26,960 likes · 624 talking about this. Samara University of Ethiopia.

Leave a Reply

Your email address will not be published.