ሰመራ ዩኒቨርሲቲ  ለአስተዳደር እና ለአካዳሚክ የስራ ሀላፊዎች  የአመራር ጥበብ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለአስተዳደር እና ለአካዳሚክ የስራ ሀላፊዎች የአመራር ጥበብ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ መስከረም 10/2015 ዓ.ም

==============================
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ ሀላፊነት ላይ ለሚገኙ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር እና የአካዳሚክ አመራሮች የአመራርነት (leadership) እሴቶችን በማስገንዘብ በአድሱ አመት የተሻለ የስራ አፈፃፀም እንድኖር የሚያግዝ ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሙያዊ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

ስልጠናው በአመራርነት ፅንሰ ሃሳብ ላይ በማተኮር ለሁለት ቀን (ከመስከረም 10 -11)፣ በእቅድ እና ሪፖርት አዘገጃጀት ዙሪያ ደግሞ ለሦስት ቀን (ከመስከረም 12-14)የሚቆይ የአቅም ማበልፀጊያ መሆኑ ተገልጿል።

ስልጠናውን ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዱረህማን ከድር ስልጠናው ለረጅም ጊዜ ሲታሰብ የነበረ መሆኑን ገልፀው ሰልጣኞች ስልጠናውን በንቃት በመከታተል ክፍተቶቻቸውን በመሙላት በቀጣይ በየስራ ክፍሎቻቸው ለመተግበር እንዲዘጋጁ ያግዛቸዋል ሲሉ ገልፀዋል።

መድረኩን ያዘጋጀው እና ያስተባበረው የዩኒቨርሲቲው የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ሲሆን የኢትዮጵያ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች ስልጠናውን እየሰጡ እንደሚገኙ ታውቋል።

በተጨማሪም በሌላ መድረክ በዩኒቨርሲቲው ለሚገኙ ሁሉም የቢሮ ፀሀፊዎች/ሴክሬታሪዎች/ በቢሮ አስተዳደር ስራ ዘርፍ ላይ ያተኮረ ስልጠና በኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች እየተሰጠ ይገኛል።

=============================

ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!
የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.