ሰመራ ዩኒቨርሲቲ  ለአስተዳደር እና ለአካዳሚክ የስራ ሀላፊዎች  የአመራር ጥበብ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለአስተዳደር እና ለአካዳሚክ የስራ ሀላፊዎች የአመራር ጥበብ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

An Exclusive joint Workshop on Ethiopia’s Strategic pursuit

Samara University in collaboration with Dire-Dawa,Addis Ababa, Jigjiga and Mekelle Universities are preparing a joint workshop on the topic of “Ethiopia’s Strategic Pursuit: Unlocking the Red Sea – A Journey through History, Geopolitics and International Law.” This workshop aims to provide a platform for scholars, researchers, policymakers, and students to explore and discuss the multifaceted […]

በዩኒቨርሲቲው ለሁለተኛው ዙር ችግኝ ተከላ የሚሆን ቅድመ ዝግጅት

በሰኔ ወር መገባደጃ ላይ የተጀመረው የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር፣ ለሁለተኛው ዙር ተከላ ከሐምሌ 10 እስከ 20/2014 ዓ.ም ለአስር ቀናት ሲከናወን ቆይቶ ዛሬ ተጠናቋል፡፡ በግብርና ኮሌጅ አስተባባሪነት በዚህ ዙር በአጠቃላይ ወደ 5ሺ የሚጠጉ ችግኞች ለመትከል መታቀዱን የገለፁት የግብርና ኮሌጅ ዲን የሆኑት መምህርት ሰአዳ አህመድ ተከላው በሚወጣው መርሃ-ግብር መሰረት የዳይሬክቶሬት ጽ/ቤቶች፣ ኮሌጆች እና ት/ቤቶች በመከፋፈል እንደሚያከናውኑት አመላክተዋል፡፡

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የ2014ዓ.ም ሁለተኛዉ ዙር የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር

ችግኝ ተከላዉን የዩኒቨርሲቲዉ አካ/ጉ/ም/ኘሬዝደንት ዶ/ር አብዱረህማን ከድር ያስጀመሩት ሲሆን የግብርና :የቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ እንዲሁም የእንስሳት ህክምና ኮሌጅ ተማሪዎች እና መምህራን ተሳታፊዎች ነበሩ። በዚህም ከ300 በላይ የብርቱካን እና የመንደሪን ችግኝ መተከሉን የግብርና ኮሌጅ የገለፀ ሲሆን በሌሎች ኮሌጆች እና ዳይሬክተሮችም የችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

“ከነሀሴ እስከ ነሀሴ”

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የአንድ አመት የለውጥ ጉዞ ስኬቶችና ተግዳሮቶች  ላይ ያተኮረ የፓናል ዉይይት

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ ሀላፊነት ላይ ለሚገኙ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር እና የአካዳሚክ አመራሮች የአመራርነት (leadership) እሴቶችን በማስገንዘብ በአድሱ አመት የተሻለ የስራ አፈፃፀም እንድኖር የሚያግዝ ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሙያዊ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

ስልጠናው በአመራርነት ፅንሰ ሃሳብ ላይ በማተኮር ለሁለት ቀን (ከመስከረም 10 -11)፣ በእቅድ እና ሪፖርት አዘገጃጀት ዙሪያ ደግሞ ለሦስት ቀን (ከመስከረም 12-14)የሚቆይ የአቅም ማበልፀጊያ መሆኑ ተገልጿል።

 

ስልጠናውን ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዱረህማን ከድር ስልጠናው ለረጅም ጊዜ ሲታሰብ የነበረ መሆኑን ገልፀው ሰልጣኞች ስልጠናውን በንቃት በመከታተል ክፍተቶቻቸውን በመሙላት በቀጣይ በየስራ ክፍሎቻቸው ለመተግበር እንዲዘጋጁ ያግዛቸዋል ሲሉ ገልፀዋል።

መድረኩን ያዘጋጀው እና ያስተባበረው የዩኒቨርሲቲው የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ሲሆን የኢትዮጵያ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች ስልጠናውን እየሰጡ እንደሚገኙ ታውቋል።

በተጨማሪም በሌላ መድረክ በዩኒቨርሲቲው ለሚገኙ ሁሉም የቢሮ ፀሀፊዎች/ሴክሬታሪዎች/ በቢሮ አስተዳደር ስራ ዘርፍ ላይ ያተኮረ ስልጠና በኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች እየተሰጠ ይገኛል።

=============================

ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!