ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለወላጅ አልባ እና አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የጀመረውን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አስቀጠለ።

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለወላጅ አልባ እና አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የጀመረውን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አስቀጠለ።

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለወላጅ አልባ እና አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የጀመረውን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አስቀጠለ።
====================================
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፡ ጥቅምት 05/2015 እ.ኢት.አ

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በጦርነት ምክንያት ወላጆቻቸውን ላጡ እና አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የሚሰጠው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በተለያዩ ወረዳዎች በመገኘት አስረክቧል፡፡

በሰመራ-ሎጊያ ከተማ ተማሪዎች የተጀመረው ድጋፍ በገዋኔ፣ ገልአሎ፣ አሚባራ እና ሀሩካ ወረዳዎች ውስጥ ባሉ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ 1,155 ተማሪዎች ድጋፍ በማድረግ ቀጥሏል።

ድጋፉ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች በመዘዋወር ለ1,500 ለሚሆኑ ተማሪዎች ሊሰጥ እንደታቀደ ተገልጿል።

ድጋፉን ያስረከቡት የዩኒቨርሲቲው የምርምር እና ፐብሊኬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ኡመር አብዱልቃድር ለተማሪዎች የምናደርገው ድጋፍ በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ተማሪዎች ከትምህርታቸው እንዳይቋረጡ በማድረግ ትውልድን በማስተማር የማህበረሰቡን ችግር መፍታት በማሰብ መሆኑን አበክረው ገልፀዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የሚያደርገውን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በቀጣዮቹ አጭር ቀናት ውስጥ በቀሩት አካባቢዎች ለሚገኙ ወላጅ አልባ ለሆኑ እና አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች እንደሚያደርስ ተብራርቷል፡፡
============================
የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.