ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1ሺ 478 ተማሪዎች አስመረቀ::

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1ሺ 478 ተማሪዎች አስመረቀ::


ሰመራዩኒቨርሲቲ ሰኔ 26/2016 – ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1ሺ 478 ተማሪዎች አስመርቋል።

ከተመራቂ ተማሪዎቹ መካከልም 450 ሴቶች እና 1ሺ 28 የሚሆኑት ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው 38 የቅድመ-ምረቃ እና 15 የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች በድምሩ በ53 ፕሮግራሞች፣ በ3 መርሃ-ግብሮች (መደበኛ:ኤክስቴንሽን እና በርቀትና ተከታታይ) ያስተማራቸውን ተማሪዎች ነው ያስመረቀው::

በምርቃት ስነ-ስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን ትምህርት ሚኒስቴር ከያዛቸው የሪፎርም ስራዎች መካከል የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በከፍተኛ ውጤት 93% በማለፍ አኩርታችሁናል። በጣም እናመሰግናለን ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ አክለውም ይህንን በጥረት ፈተናን የማለፋችሁን ተሞክሮ በቀጣይ በስራው አለም የሚገጥማችሁን ችግር ሁሉ ለማለፍ ለለውጥ እንደምትጠቀሙበት እምነቴ ከፍያለ ነው ብለዋል።

ለዚህ ውጤት መመዝገብ የመምህራን፣ የድጋፍ ሰጪው እና የእናንተም ጥረት ከፍተኛ ነውና እናመሠግናለን ሲሉ ተናግረዋል::

የዛሬውን ምረቃ ልዩ የሚያደርገው 51% የሚሆኑት ተመራቂዎች በልህቀት መስካችን መሆናቸው ሲሆን ይህም እየሄድንበት ያለው መንገድ ትክክል መሆኑን ያሳያል ብለዋል::

በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሠረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ ባደረጉት ንግግር ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ሚኒስቴር የለውጥ ስራወችን ለመተግበር የሰጠውን ትኩረት በጎ ነው ሲሉ ገልጸዋል::

የቱሪዝም ሚኒስተር ዲኤታ እና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ስለሽ ግርማ ከእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በኃላ ዩኒቨርሲቲው የአፕላይድ ዩኒቨርሲቲ ቁመና ለመያዝ የጀመራቸው ስራወች ጥሩ መሆናቸውን ጠቁመው የልህቀት መስኮቹ (ቱሪዝም:ግብርና እና ማእድን ላይ አተኩሮ መስራቱን እንዲቀጥል አሁን በልህቀት መስኮች ላይ የተመዘገበው የመውጫ ፈተና ስኬት ተጠናክሮ እንድቀጥል ሲሉ
በአፅንኦት ተናግረዋል::

የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባላት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ፣ አቶ አብዱልሃሚድ መሐመድ ፣ ፕ/ር ሸለመ በየነ እንድሁም የክልል የስራ ሀላፊዎች በክብር እንግድነት ተገኝተዋል::

ከየትምህርት ክፍላቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሜዳልያ የተበረከተላቸው ሲሆን ተማሪዎች በቆይታቸው በቀሰሙት እውቀት ሀገርና ህዝባቸውን በታማኝነትና በቅንነት እንዲያገለግሉ መልዕክት ተላልፏል፡፡

 • ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!
  =================
  ✍️የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ
  Follow,Share and like our social media pages.
  ፌስቡክ👇
  https://www.facebook.com/susamara2008/
  ቴሌግራም👇
  https://t.me/SamaraUniversityEthiopia
  ዩትዩብ👇
  https://youtube.com/channel/UCvDWGawVYKQa_FJY8supkBA?sub_confirmation=1
  ዌብሳይት👇
  Www.su.edu.et
  ትዊተር👇
  https://twitter.com/SamaraunivEthio?t=QlDpWx8vlY_udWdGAztwvg&s=09
  ሊንክድን👇
  https://www.linkedin.com/company/semara-university/
  ቲክቶክ👇
  https://www.tiktok.com/@samara.university?_t=8ipUGAsrMwg&_r=1

Leave a Reply

Your email address will not be published.