ሰመራ ዩኒቨርሲቲ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በመተባበር ተንቀሳቃሽ የእንስሳት ህክምና ፕሮጀክት የማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሄዱ።

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በመተባበር ተንቀሳቃሽ የእንስሳት ህክምና ፕሮጀክት የማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሄዱ።

 

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በመተባበር ተንቀሳቃሽ የእንስሳት ህክምና ፕሮጀክት(mobile Veterinary Project)   የማስጀመሪያ ፕሮግራም በጭፍራ ወረዳ ወአማ  አካባቢ ላይ በመገኘት አካሄዱ።

የማስጀመሪያ ፕሮግራሙ በጣም ውጤታማ እንደነበር በመግለፅ የዚህ ፕሮጀክት  ትኩረት ሁለቱ አጎራባች ዩኒቨርሲቲዎች የአፋር እና አማራ   ክልል በሚዋሰኑበት አካባቢ የሚኖሩ የአርብቶ አደር ማህበረሰብ እንስሳትን እስከ መኖሪያ ቀያቸው ድረስ በመሄድ የክትባት እና የጠቅላላ ህክምና አገልግሎቶችን በመስጠት: ማህበረሰቡ ከእንስሳቱ ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኝ ማስቻል ስለሆነ  አጠናክረን እንሠራለን ያሉት የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ወኪል ም/ፕሬዚዳንት አደም አሊ ናቸው።

አካባቢው በርካታ እንስሳት የሚገኙበት እንደመሆኑ መጠን በገበያ እና በግጦሽ ሁል ጊዜ ስለሚገናኙ ለተላላፊ በሽታዎች ተጋላጭ ስለሚሆኑ ከህክምና ይልቅ የመከላከል ክትባት ላይ አተኵረን እንሠራለን ሲሉ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ.ር አማረ ቢሆን ተናግረዋል። 

አገልግሎቱ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን በዛሬው መርሃ ግብር የሁለቱም ዩኒቨርሲቲዎች ባለሙያዎች ከ1000 በላይ  እንስሳትን ማከም መቻላቸው ተገልጽል::

በቀጣይ ሌሎች ተባባሪ አካላትን በማሳተፍ በአጎራባች አካባቢዎች በጥናትና ምርምር የተደገፈ የቅድመ መከላከል  አገልግሎት እንደሚሰጥ የገለፁት የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር መሀመድ አህመድ ያሲን ናቸው ::

==============

የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.