በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ ፈተና አስፈፃሚዎች  በአፍምቦ ሀይቅና ገመሪ ሀይቅ ጉብኝት ላይ

በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ ፈተና አስፈፃሚዎች በአፍምቦ ሀይቅና ገመሪ ሀይቅ ጉብኝት ላይ

በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ ፈተና አስፈፃሚዎች የሁለተኛ ዙር የጉብኝት ፕሮግራም ተዘጋጀ።

በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ ፈተና አስፈፃሚዎች የሁለተኛ ዙር የጉብኝት ፕሮግራም ተዘጋጀ።
====================================
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፡ ጥቅምት 12/2015 እ.ኢት.አ

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የ2014/2015 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለማስፈፀም ለተሳተፉ የፈተና ግብረ-ሃይል ለ2ኛ ጊዜ የጉብኝት ፕሮግራም አዘጋጀ፡፡

ጉብኝቱ ከጥንታዊቷ አይሳኢታ ከተማ ጀምሮ የአዋሽ ወንዝ መዳረሻ እስከሆነው አፍአምቦ ሀይቅ ድረስ ሲሆን በተጨማሪም በተለያዩ የሀገራችን መንግስታቶች እና የውጭ ወራሪዎች ከ1883 እስከ 1983 ሲጠቀሙበት የነበረ ታሪካዊ ቦታ ጎብኝተዋል። ባዩት ነገርም በጣም እንደተደመሙ ገልፀዋል።

ጎብኝዎቹ በጉብኝታቸው አፋር ብዙ የቱሪስት መስህብ እና መልማት የሚችል እምቅ ሃብት እንዳላት አብራርተው ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ይህንን ሃብት የማህበረሰቡን ኑሮ የሚያሻሽል እንድሆን ጥናት በመስራት ማገዝ እንደሚጠበቅበት ጠቁመዋል።

ቱሪዝም ለሰመራ ዩኒቨርሲቲ አንዱ የልህቀት አቅጣጫው በመሆኑ ዘርፉን በተግባር ለማስተዋወቅና ጥናትና ምርምር ለመስራት ለሚሹ ምሁራን በሩ ክፍት እንደሆነ ተገልጿል።
============================
የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.