በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ግቢ በህብረት የፅዳት ዘመቻ ተከናወነ።

በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ግቢ በህብረት የፅዳት ዘመቻ ተከናወነ።

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፡ጥቅምት 21 ቀን 2016 ዓ.ም

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ጥቅምት 28/2016 የሚቀበላቸውን ነባር ተማሪዎች ምክንያት በማድረግ የግቢ ፅዳት ዘመቻ ተደርጓል፡፡

የፅዳት ዘመቻውን:የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ አመራሮች፣የት/ርት ሚኒስቴር ሱፐርቪዥን አባላት እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ፣
የሰሜን ምስራቅ እዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም በግቢው ውስጥ በተለያዩ የኮንስትራክሽን ስራ የተሰማሩ ሰራተኞች በጋራ በመሆን ነው ያከናወኑት።

“መከላከያ ህይወቱን አስይዞ ሀገርን የሚጠብቅ የሀገር መከታ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ይህ ስራ ለእነሱ በጣም ቀላሉ ተግባር ቢሆንም ለዩኒቨርሲቲው ግን ትልቅ ክብር ነው። ዩኒቨርሲቲውም ለዚህ ትልቅ ተግባራችሁ ከልብ ያመሰግናችኋል” ሲሉ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው የፀዳ መሆኑ የተቋሙን ደህንነት እና የተማሪዎችን ጤና ለመጠበቅ የሚያስችል ከመሆኑም በላይ ተማሪዎቻችንን በደማቅ ሁኔታ ለመቀበል የታሰበ በመሆኑ ዘመቻዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል ።

መከላከያ ሀገር በምትፈልግበት ቦታ ሁሉ በመገኘት የሚጠበቅበትን ሃላፊነት የሚወጣ መሆኑን ገልፀው፣በሰመራ ዩኒቨርሲቲ በመገነኘት የሰሩት ግቢውን የማፅዳት ተግባር እጅግ እንዳስደሰታቸው የገለፁት ደግሞ ከሰሜን ምስራቅ እዝ ኮሎኔል አስጨናቂ ደመቀ ናቸው፡፡

ኮሎኔሉ አያይዘውም መከላለያ በሚገኝበት አካባቢ ሁሉ በተለያዩ የልማት ስራዎች መሳተፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
===============
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.