በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መካከል የሚደረገው የእግር ኳስ ጨዋታ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ተካሄደ::

በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መካከል የሚደረገው የእግር ኳስ ጨዋታ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ተካሄደ::

በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መካከል የሚደረገው የእግር ኳስ ጨዋታ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ተካሄደ::
==============
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ:የካቲት 12/2016 ዓ.ም
ዩኒቨርሲቲው በየአመቱ የሚካሄደውን የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት በማስመልከት በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መካከል የስራ ዘርፎችን መሰረት ያደረጉ 8 የእግር ኳስ ቡድኖች የተቋቋሙ ሲሆን: ከዛሬ የካቲት 12 ጀምሮ እስከ የካቲት 30/2016 ዓ.ም ድረስ በወጣላቸው መርሃግብር መሰረት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ::
የመክፈቻ ጨዋታው ዛሬ በፕሬዚደንት ፅ/ቤት እና በማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ መካከል ተደርጎ: የፕሬዚደንት ፅ/ቤት 3-1 ማሸነፍ ችሏል::
የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝዳንት ጨምሮ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች፣ከክልል የተጋበዙ እንግዶች እንዲሁም የግቢው ማህበረሰብ በተገኘበት ጨዋታው በይፋ ተጀምሯል::
መላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን ስፖርት ለጤንነት:ለአንድነት:ለመዝናናትና መሰል ጥቅሞቹ ሲል በጨዋታዎች እየተሳተፈና እየደገፈ ይገኛል: በማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት ፕሮግራሞችም ላይ በንቃት ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል::
================
ማህበረሰቡን እናገለግላለን !!!
ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ

Leave a Reply

Your email address will not be published.