በዩኒቨርሲቲው የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የድጋፍና ክትትል የሱፐርቪዥን መርሃ-ግብር

በዩኒቨርሲቲው የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የድጋፍና ክትትል የሱፐርቪዥን መርሃ-ግብር

በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ቀን ሲካሄድ የቆየው የ2016 ዓ.ም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብር በርካታ የመስክ ምልከታዎችን እና  ጥልቅ ውይይቶችን በማድረግ ተጠናቋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የሱፐርቪዥን ቡድን በምልከታው በ2015 ጥሩ አፈፃፀም ያላቸው ፕሮጀክቶች፣ ጉድለት ያለባቸው እና እየተወሰዱ ያሉ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማድመጥ፣ ከዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ካውንስል ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

 የሱፐርቪዥን ቡድኑ በመስክ ምልከታ ተዟዙሮ  ያየውን እና በየደረጃው ከሰራተኞች ጋር ከተደረጉ ውይይቶች ያገኛቸውን ሃሳቦች ለዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር አቅርቦ መወሰድ የሚገባቸውን እርምቶች ጠቁሟል። 

በመጨረሻም ቡድኑ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር እየተከተለው ያለው የአመራር ጥበብ፣በሰራተኛው ውስጥ የተገነዘብነው ተቋሙን የኔ ብሎ የመስራት ተነሳሽነት እንድሁም የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ከማስደነቅም በላይ ለመሰል ተቋማት አርአያ የሚሆን ስራ እና ስርአት እንዳላችሁ ተመልክተናል ሲሉ  ገልፀዋል። 

የዩኒቨርሲቲው አመራርም የተሰጠውን ምክረ ሀሳቦች ተቀብሎ በቀጣይ ሰፊ ስራዎችን እንደሚሰራ አብራርቷል።

==============

ህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ

ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.