ነባር ተማሪዎችን ለመቀበል በመሰራት ላይ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተገመገሙ

ነባር ተማሪዎችን ለመቀበል በመሰራት ላይ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተገመገሙ

ነባር ተማሪዎችን ለመቀበል በመሰራት ላይ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተገመገሙ።
====================================
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፡ ጥቅምት16/2015 እ.ኢት.አ

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት ነባር ተማሪዎቹን ተቀብሎ የመማር ማስተማር ስራውን ለማስቀጠል እየተከናወነ ያለውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ገምግሟል።

እንደ ዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ግምገማ ከሆነ የ2015 መደበኛ ነባር ተማሪዎቹን ለመቀበል የሚያስችል ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሏል።

ማኔጅመንቱ በመስክ ምልከታው የመማሪያ ክፍሎችን፣ የመመገቢያ አዳራሾችን እና የመኝታ አገልግሎቶች ያሉበትን አሁናዊ ዝግጁነት ተዘዋውሮ አይቷል።

በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው ጥቅምት 21 እና 22 2015 ዓ.ም የ1ኛ አመት ነባር ተማሪዎችን እንድሁም ህዳር 01 እና 02/2015 ዓ.ም የ2ተኛ አመት ተማሪዎችን እና ከዚያ በላይ ያሉ ተማሪዎችን ለመቀበል ወስኗል።

የዩኒቨርሲው ፕሬዝዳንት ወኪል እና የአስተዳደር ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ሁሴን ኡመር (ዶ/ር) በግምገማው ወቅት ለተማሪዎች ቅበላ የሚያስፈልጉ ቀሪ ዝግጅቶች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው እንድከናወኑ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ትምህርት ለማስጀመር ያለው ጊዜ በጣም አጭር በመሆኑ እየተደረገ ያለው ዝግጅት ከዚህ በላይ ፈጥኖ መሰራት እና ቀድሞ መጠናቀቅ እንደሚገባው የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር እና የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ወኪል ሳሊህ አህመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የቅድመ ዝግጅት ትግበራ የመማር ማስተማር ስራውን ለማሳለጥ እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ ሃላፊነት ወስዶ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግም ተገልጿል።

====================================
የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.