አለም አቀፍ የሳይንስ ቀን አስመልክቶ በተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ስራ ውድድር ተካሄደ

አለም አቀፍ የሳይንስ ቀን አስመልክቶ በተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ስራ ውድድር ተካሄደ

አለም አቀፍ የሳይንስ ቀን አስመልክቶ በተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ስራ ውድድር ተካሄደ

…………………………………………………………………………

ጥቅምት 29/2015 ዓም. ትምህርት ሚኒስቴርና አጋር ድርጅቶች በመተባበር ለ7ኛ ጊዜ የሚከበረውን አለም አቀፍ የሳይንስ ቀን አስመልክቶ በተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ስራ ውድድር አካሂደዋል።

ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች እና የክልል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ መምህራንና ተማሪዎች የፈጠራ ስራዎቻቸው ለዳኞች ገለጻ በማድረግ አስገምግመዋል።

የውድድሩ ውጤትም በአውደ ርእዩ መዝጊያ ወቅት እንደሚገለጽና ከየምድቡ ከአንድ እስከ ሦስት ለወጡ ተወዳዳሪዎች የማበረታቻ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ተገልጿል።

አውደ ርእዩም በነገው እለት ለህዝብ ክፍት በመሆኑ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ግቢ በመገኘት መጎብኘት እንደሚቻል ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.