አመታዊ የሚድ፣ላርጅ እና የሜጋ ስኬል የምርምር ፕሮፖዛሎች ግምገማ ወርክሾፕ ተካሄደ ።

አመታዊ የሚድ፣ላርጅ እና የሜጋ ስኬል የምርምር ፕሮፖዛሎች ግምገማ ወርክሾፕ ተካሄደ ።

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ  የምርምር እና ቴክኖሎጅ ሽግግር ም/ፕሬዚደንት ጽ/ቤት የዓመታዊ የሚድ፣ላርጅ እና  ሜጋ ስኬል የምርምር ፕሮፖዛሎችን መገምገሚያ  ወርክሾፕ አካሂዷል።

ለግምገማ የቀረቡት በአጠቃላይ 22 ፕሮፖዛሎች ሲሆኑ፣14 የሚድ እና 2 የላርጅ ስኬል ፕሮፖዛሎች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 6ቱ የሜጋ ስኬል ፕሮፖዛሎች ናቸው፡፡

የምርምር ፕሮፖዛሎቹ በዋናነት ተግባር ተኮር ምርምሮች ሲሆኑ፣ በዩኒቨርሲቲው የትኩረት መስኮች  በተለይ በግብርና እና በማእድን እንዲሁም በሰውና በእንስሳት ጤና፣ በወሳኝ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

የወርክሾፑ አላማ ሁሉም የምርምር ፕሮፖዛሎች ወደ ዋናው የምርምር ስራ ከመገባቱ በፊት፣ከሳይንሳዊ የምርምር ሂደቶች፣ከአዋጭነት እና ለማህበረሰብ ዕድገት ከሚኖራቸው ፋይዳ አንፃር፡ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተጋበዙ ተመራማሪዎች እና በዩኒቨርሲቲው ምሁራን ተገምግመው፣ተተችተው እና አስተያየት ተሰጥቶባቸው እንዲያልፉ ለማድረግ ነው ተብሏል።

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ መጠን የምርምር ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ ወደ ማህበረሰብ አገልግሎት ተቀይረው የህዝቡን ኑሮ በተጨባጭ ለማሻሻል የሚያግዙ እንዲሆኑ ታቅዶበት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

=================

ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!

የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ

Leave a Reply

Your email address will not be published.