አዲሱ የስራ አመራር ቦርድ ዩኒቨርሲቲውን ከጎበኘ በኋላ ከማኔጅመንት ካውንስል አባላት ጋር ውይይት አደረገ።

አዲሱ የስራ አመራር ቦርድ ዩኒቨርሲቲውን ከጎበኘ በኋላ ከማኔጅመንት ካውንስል አባላት ጋር ውይይት አደረገ።

አዲሱ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ዩኒቨርሲቲውን ከጎበኘ በኋላ ከማኔጅመንት ካውንስል አባላት ጋር ውይይት አደርጓል።

አድሱ የስራ አመራር ቦርድ ከዩኒቨርሲቲው የትኩረት መስክ ጋር ተመሳሳይ የትምህርት ዝግጅት ያላቸው፣ በተለያየ የሃላፊነት ቦታ ላይ የሰሩ እና ተቋማትን በብቃት የመሩ አባላት ስብጥር በመሆኑ የተሻለ ስራ ይሰራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የቦርዱ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ስለሺ ግርማ ገልፀዋል።

የስራ አመራር ቦርዱ በዩኒቨርሲቲው እየተገነቡ ያሉ የግንባታ ፕሮጀክቶች ያሉበትን ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል። በዚህም የቦርድ አባላቱ ተጀምረው የተቋረጡ ፕሮጀክቶችን በማየት የሚቀጥሉበትን እና ተጠናቀው አገልግሎት በሚሰጡበት መንገድ ላይ ውሳኔ እንደሚሰጡ እና የ2015 እቅድን በመገምገም እንደሚያፀድቁ የቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ስለሺ ግርማ ተናግረዋል።

በውይይቱ ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ቀርበው በዩኒቨርሲቲው አመራሮች ምላሽ ተሰቶባቸዋል።

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ እተገብራቸዋለሁ ብሎ የያዛቸውን እቅዶች ከግብ እንዲያደርስ ከጎኑ ሁነው እንደሚያግዙ የቦርድ አባላቱ በውይይቱ ወቅት ገልፀዋል፡፡

**

የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!