“አድዋን ለጠንካራ ሀገረ-መንግሰት ግንባታ”

“አድዋን ለጠንካራ ሀገረ-መንግሰት ግንባታ”

ዩኒቨርሲቲው”አድዋን ለጠንካራ ሀገረ-መንግሰት ግንባታ”በሚል መሪ ሀሳብ                              ሀገራዊ የምክክር መድረክ አካሄደ።
==================
                     ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ጥር 14/2016 ዓ.ም

                ሰመራ ዩኒቨርሲቲ “አድዋን ለጠንካራ ሀገረ-መንግሰት ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ ያዘጋጀው ሀገራዊ የምክክር መድረክ በደማቅ ሁኔታ ተከናውኗል ።


                    የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን በመክፈቻ ንግግራቸው በአድዋ የተገኘውን ድል ለጠንካራ ሀገረ-መንግስት ግንባታ:ለሰላምና ለልማት እንጠቀምበት በሚል ሀሳብ የተዘጋጀውን መድረክ ለመካፈል ስለመጣችሁ እጅግ እናመሰግናለን ሲሉ ለእንግዶች አቀባበል አድርገዋል::

                           ፕሬዚዳንቱ በማስከተልም “ዩኒቨርሲቲያችን ከመማር ማስተማርና ምርምር ስራዎቹ ባለፈ ለሀገር ግንባታና አብሮነት ግብአት የሚሆኑ መድረኮችን በተደጋጋሚ በማዘጋጀት ይታወቃል: የአድዋ ወርክሾፕም የበኩላችንን አስተዋፅዖ የምናበረክትበት በመሆኑ ለጋራ ሀገራችን የየራሳችንን ሀሳብ ማዋጣት ይገባናል” ሲሉ ተናግረዋል::

                    የእለቱ የክብር እንግዳ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሠላም ሚኒስቴር ሚኒስተር ዴኤታ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ በንግግራቸው እንደገለፁት አድዋን ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ -መንግስት ግንባታ ብሎም ሀገራዊ እሴቶቻችንን ለማጎልበት እንደ እድል መጠቀም አለብን: እኛ ባህላዊ እሴቶቻችንን በቤተሰብ ደረጃ ገንብተን የመጣን ህዝቦች በመሆናችን አድዋን እንደ ተምሳሌት ወስደን የሀገራዊ ጥቅሞቻችን ማስጠበቂያ መሳሪያ መሆን አለበት ብለን እናምናለን ሲሉ አብራርተዋል።

                                           የክብር እንግዶች የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስተር ዲኤታ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ እንዲሁም የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ፣ የክልል አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች፣ የሃይማኖች አባቶች ፣ የUገር ሽማግሌዎች፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ተወካዮች ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት እና ተማሪዎች ተሳትፈውበታል።

                                      በመድረኩ ለውውይት መነሻ ፅሑፍ በፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ ሙክታር ጦይብ ቀርቦ ሰፊ ውይይት በተሳታፊዎች የተካሄደ ሲሆን: በተጨማሪም የተለያዩ አድዋን የሚዘክሩ የጥበብ ስራዎች በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች (ድንቅ ቲም) አባላት ቀርበዋል።

 

                        መድረኩ አሁን ላለው ትውልድ የሀገር ፍቅር ስሜት የሚፈጥር እና የተከበረች እና የበለፀገች ሀገርን በቀጣይነት ለመገንባት ብሎም ለማረጋገጥ ወሳኝ ግንዛቤ እንደሚፈጥርም ተገልጿል።

====================
ህዝብና በአለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
ማህበረሰቡን እናገለግላለን ! 

Leave a Reply

Your email address will not be published.