ዓለም አቀፍ የነጭ ሪቫን ቀን በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ

ዓለም አቀፍ የነጭ ሪቫን ቀን በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በሀገር ደረጃ ለ18ኛ ጊዜ “መቸም የትም በምንም ኹኔታ ጾታዊ ጥቃትን ዝም አንበል” በሚል መልእክት እየተከበረ የሚገኘውን አለም አቀፍ የነጭ ሪቫን ቀን በኤች.አይቪ ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር፣ የሴቶች ጥቃትን በመከላከል እና የአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረታቸውን ባደረጉ ዝግጅቶች አከበረ፡፡

ቀኑን የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የሴቶችና ማህበራዊ አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ እና የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያዎች ማህበር ሰመራ ቅርንጫፍ በጋራ በመሆን እንዳዘጋጁት በመድረኩ ተገልጿል፡፡

በመርሃ-ግብሩ በኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከል እና በአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ላይ የተዘጋጁ ሁለት ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበዋል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ማህበር ሰመራ ቅርንጫፍ ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ እና ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ባለሙያ ጋር በሴቶች ጥቃት ምንነት፣ መገለጫዎቹ እና የአካል ጉዳተኞች ላይ ያተኮረ ፓናል ውይይት አከናውኗል፡፡

በዝግጅቱ የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች፣ ተማሪዎች እና ተጋባዥ እንግዶች የተገኙ ሲሆን በቀረቡ ጥናታዊ ጽሁፎች እና ፓናል ውይይት ሃሳብ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያቶች ምላሽ በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡ 

ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!

የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ

Leave a Reply

Your email address will not be published.