ዘመናዊ የንብረት አስተዳደር ሶፍትዌር ስልጠና እየተሰጠ ነው

ዘመናዊ የንብረት አስተዳደር ሶፍትዌር ስልጠና እየተሰጠ ነው

ዘመናዊ የንብረት አስተዳደር ሶፍትዌር ስልጠና እየተሰጠ ነው።

ዘመናዊ የንብረት አስተዳደር ሶፍትዌር ስልጠና እየተሰጠ ነው።
==========================
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ህዳር 05/2015 ዓ.ም

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለንብረት ክፍል አመራሮችና ሰራተኞች በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ የንብረት አስተዳደር ሶፍትዌር ስልጠና ከቅዳሜ ህዳር 03/2015 ዓም ጀምሮ በመስጠት ላይ ነው።

ስልጠናው የሚሰጡት የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የንብረት አስተዳደር ሶፍትዌርን ያበለጸጉ ባለሙያዎች ሲሆኑ፣ ሰልጣኞች ዘመናዊ የንብረት ቁጥጥር ጥበብን በመገንዘብ የተሻለ የስራ አፈፃፀም እንድኖራቸው የሚያግዝ ሙያዊ ስልጠና እንደሆነም ታውቋል።

ስልጠናውን ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሁሴን ኡመር ሲሆኑ፣ ስልጠናው ለረጅም ጊዜ በተበታተነ መንገድ ሲሰራበት የነበረውን የንብረት አያያዝና ቁጥጥር ወደ ዲጅታል ስርአት በመቀየር፣ የመንግስት ንብረት ብክነትን እና ወጭን ለመቀነስ የሚያስችል እንዲሁም የንብረት አስተዳደር አሰራርን የሚያዘምን እና ስንቸገርባቸው የነበሩ አገልግሎቶችን የሚያቀላጥፍ መሆኑን ገልፀዋል።

በመጨረሻም ዩኒቨርሲቲው በቴክኖሎጂ የሚታገዘውን የንብረት ምዝገባና ቁጥጥር ለማስፈፀም ቆርጦ መነሳቱን ገልፀው፣ ሰልጣኞች ስልጠናውን በንቃት በመከታተል፣ የሚቀስሙትን እውቀት በቀጣይ በየስራ መደቦቻቸው ለመተግበር እንዲዘጋጁ አሳስበዋል።

ይህ የንበረት አስተዳደር ሶፍተዌር በቀጣይ ወር ሙሉ በሙሉ ወደ ትግበራ የሚገባ ሲሆን የንበረት ምዝገባ፣ ወጭ፣ ማስወገድ፣ ዝውውር፣ ቆጠራ፣ ክሊራንስ እና የመሳሰሉ ስራዎች አውቶሜት የሚደረጉ መሆኑን ሶፍተዌሩን ካበለጸጉ ባለሞያዎች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
======================
ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!

የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Leave a Reply

Your email address will not be published.