የምርምርና የቴክኖሎጂ ስራ ውጤቶች ማሳያ አውደጥናት ተካሄደ::

የምርምርና የቴክኖሎጂ ስራ ውጤቶች ማሳያ አውደጥናት ተካሄደ::


ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሰኔ 6/2016 ዓ.ም
በሰመራ ዩኒቨርሲቲ:የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚደንት ፅ/ቤት:የኢንዱስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ተመራማሪ መምህራንን እና ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች ፕሮፖዛሎች በማወዳደርና በመደገፍ ያሰራቸውን ያለቀላቸው የቴክኖሎጂ ፕሮጀክቶች ማሳያ አውደ ጥናት አካሂዷል።

የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተ/ም/ፕሬዝዳንት አደም ዓሊ እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው ወደ ተግባር ተኮር (Applied University) በሽግግር ላይ እንደመሆኑ መጠን በተጨበጭ የሚታዩ ችግር ፈቺና ኑሮን የሚያሻሽሉ የቴክኖሎጂ የምርምር ውጤቶችን በማቅረብ የማህበረሰብ አጋርነቱን እያሳየ ነው: በቀጣይም በሂደት ላይ ያሉ ስራወች እንደሚቀርቡ ገልፀዋል።

ዛሬ ከቀረቡት አራት የቴክኖሎጂ የምርምር ስራዎች መካከል በቻርጅ የሚሰራ ብስክሌት፣ በቤት ውሰጥ በቀላሉ ሊሰራ የሚችል የመጠጥ ውሃ ማጣሪያ፣ የፀረ-ተባይ መከላከያ እንዲሁም የበቆሎ ምርት መፈልፈያ ማሽን ይገኙበታል::

በመድረኩ ከፍተኛ አመራሮች፣ ከህብረተሰቡ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ ተመራማሪዎች እና ተማሪዎች ተገኝተዋል።
#ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!
=================
✍️Public Relations Executive
Follow,Share and like our social media pages.
ፌስቡክ👇
https://www.facebook.com/susamara2008/
ቴሌግራም👇 https://t.me/SamaraUniversityEthiopia
ዩትዩብ👇 https://youtube.com/channel/UCvDWGawVYKQa_FJY8supkBA?sub_confirmation=1
ዌብሳይት👇
Www.su.edu.et
ትዊተር👇
https://twitter.com/SamaraunivEthio?t=QlDpWx8vlY_udWdGAztwvg&s=09
ሊንክድን👇
https://www.linkedin.com/company/semara-university/
ቲክቶክ👇
https://www.tiktok.com/@samara.university?_t=8ipUGAsrMwg&_r=1

Leave a Reply

Your email address will not be published.