የሠመራ ዪኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት: በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

የሠመራ ዪኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት: በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

****************************************

President of Samara University held a Discussion with the French Ambassador to Ethiopia.
********
Samara University: October 07, 2022

The President of Samara University, Dr. Muhammad Usman, held a discussion with the French Ambassador to Ethiopia, Mr. Remy Marichaud , in Addas Ababa.

As per their discussions, both parties have agreed to work together on capacity building, technology transfer, educational opportunities and trainings, focusing on Samara University’s areas of excellence : mining, tourism and dryland agriculture.

On his part, H. E Ambassador Remi emphasized the importance of creating a tripartite relationship among Samara University, University of Djibouti and the French Embassy and confirmed his readiness to creat a linkage between Samara University and academic institutions in France.

The two parties also discussed the importance of opening French Corner at Samara University for the exchange of French-related research and information and providing French language services.

Samara University will soon participate in the French higher education institutions fair that will be held in Addis Ababa.
***********
Public and International Relations Directorate
We serve the community!!!

 

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ: ጥቅምት/28/2015 ዓ.ም

የሠመራ ዪኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር መሐመድ ኡስማን በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሚስተር ሬሚ ማሪሾ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት በአድስ አበባ አድርገዋል።

በውይይታቸው የጋራ ግንኙነት በመፍጠር በአቅም ግንባታ፣በቴክኖሎጅ ሽግግር፣ በትምህርት እድልና ስልጠናዎችን በማመቻቸት እንድሁም የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የልህቀት አቅጣጫወች በሆኑት ማዕድን፣ቱሪዝም እና ግብርና ላይ በማተኮር በምርምር የተደገፉ ስራዎችን በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

በተጨማሪም ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ከጅቡቲ ዩኒቨርሲቲ እና የፈረንሳይ ኤምባሲ ጋር የሶስትዮሽ ግንኙነት በመፍጠር በጋራ ለመስራትም የተስማሙ ሲሆን፣ሰመራ ዩኒቨርሲቲ እና ጅቡቲ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመስራት በቅርቡ መፈራረማቸው የሚታወስ ነው።

አምባሳደር ሬሚ በበኩላቸው በሀገራቸው የሚገኙ የምርምር ተቋማትን፣ ምሁራንን እና ቴክኖሎጂዎችን በማስተሳሰር በጋራ ለመስራት አስቻይ ሁኔታወች እንደሚመቻቹ ገልፀው፣ አንድ የፒ.ኤች.ዲ የትምህርት እድል እንደሰጡና በቀጣይ ሌሎች እድሎችም እንደሚኖሩ ገልፀዋል።

በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለጥናትና ምርምር፣ፈረንሳይን የተመለከቱ መረጃዎች ልውውጥ እና የፈረንሳይኛ ቋንቋ አገልግሎቶች የሚሰጡበት ማዕከል ( ፍሬንች ኮርነር ) መክፈት አስፈላጊ እንደሆነም በማንሳት ተወያይተዋል።

በመጨረሻም ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ በሚካሄደው የፈረንሳይ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኤግዚቢሽን ላይ ተሳታፊ እንደሚሆንም ተገልጿል።

**************************************
ህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.