የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል ተማሪዎች በ8ኛ አገር አቀፍ የሳይንስና ኢንጂነሪንግ ውድድር ላይ ተሸላሚ ሆኑ::

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል ተማሪዎች በ8ኛ አገር አቀፍ የሳይንስና ኢንጂነሪንግ ውድድር ላይ ተሸላሚ ሆኑ::

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው በ8ኛው ሀገር አቀፍ የሳይንስና ኢንጂነሪንግ ውድድር (8th annual National Science and Engineering Fair) ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈ ሲሆን፣ተማሪዎች የሰሯቸውን የፈጠራ ስራዎች አቅርበው ተሸላሚም ሆነዋል::

ውድድሩ በሀገራችን ካሉት 30 ስቴም ማዕከላት ተማሪዎች የተሳተፉበት ሲሆን: የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል ተማሪ ረውዳ መሀመድ እና ጓደኞቿ በሰሩት “Flood Alert system” ፕሮጀክት አንደኛ በመውጣት አሸናፊ በመሆን የላብቶፕ  እና የ10,000 ብር ተሸላሚ ሆነዋል::

በተጨማሪም በሌሎች የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል  ተማሪዎች የተሰሩ ፕሮጀክቶች የፈጠራ ባለቤትነት(patent) ምዝገባ እና  እውቅና እንደሚያገኙ ተገልጿል፡፡

ለውጤቱ መመዝገብ አስተዋፅኦ ላደረጉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የኢንደስትሪ ትስስር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት:የስቴም ፖወር ማዕከል አመራሮች፣ መምህራኖች እንዲሁም ተማሪዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ  የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ወ/ም/ ፕሬዚዳንት አደም አሊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

=============

የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ

ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.