የሰመራ ዩኒቨርሲቲ እግርኳስ ክለብ አዳዲስ አሰልጣኞችን አስፈረመ።

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ እግርኳስ ክለብ አዳዲስ አሰልጣኞችን አስፈረመ።

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ እግርኳስ ቡድን ለተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች አዳዲስ አሰልጣኞችን አስፈርሟል።

በዚሁ መሰረት ኤፍሬም እሸቱለክለቡ ዋና አሰልጣኝ፣ኤፍሬም ሰይድ ም/ዋና አሰልጣኝ፣ አሊ ሀንፈሬ ም/አሰልጣኝ፣
ሚፍታህ ወግሪስ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ፣ተሰማ እውነቴ የቴክኒክ ዳይሬክተር  በመሆን ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡

ከአሰልጣኞቹ ጋር የተፈራረሙት የክለቡ ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አብዱረህማን ከድር ክለቡ በክልሉ ብቸኛ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲውን እና ክልሉን በመወከል ብቃት ያላቸው ወጣት ተጫዋቾችን በማፍራት፣በሀገር አቀፍ ደረጃ ጠንካራና ተፎካካሪ እንዲሆን እየተሰራ ነው ብለዋል።

በማስከተልም ዩኒቨርሲቲው ክለቡ በገቢ ራሱን እንድችል የሰራተኞችን ካፍቴሪያ እንድሰራበት መስጠቱን ገልፀው የክለቡ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች የግመል ስነ-ልቦና እና ጥንካሬ እንድኖራቸው ሁላችንም ድጋፍ ማድረግ አለብን ሲሉ መልክት አስተላልፈዋል።

ፈራሚዎቹ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ክለቡን ጠንካራ ለማድረግ እያደረገው ያለው ጥረት የሚደነቅ ነው፣የዚህ ክለብ አባል በመሆናችን ደስተኛ ነን ብለዋል፡፡
===============
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.