የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት የሁለተኛ ሩብ አመት እቅድ ግምገማ አካሂዷል።

የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት የሁለተኛ ሩብ አመት እቅድ ግምገማ አካሂዷል።

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የአካደሚክ ጉዳዮች ም/ ፕሬዚዳንት  ጽ/ቤት የ 2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መደበኛ ት/ርት መጀመርን በማስመልከት የሁለተኛ ሩብ አመት እቅድ ግምገማ አካሂዷል።

በመድረኩ የአካዴሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ.ር አብዱረህማን ከድር ከ Comprehensive ወደ Applied science ዩኒቨርሲቲ ሽግግርን አስመልክቶ በጀርመን ዩኒቨርሲቲዎች ፣ እንዲሁም በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች በ (Leadership Management and Governance) ዙሪያ የቀሰሙትን ልምድ  ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሊጠቀምባቸው በሚችለው የተመረጡ ተሞክሮዎች ላይ ትኩረት አድርገው ለአካደሚክ ማህበረሰቡ አቅርበዋል።


በተጨማሪም በመሻሻል ላይ የሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሌጅስሌሽን (Senate Legislation) ለአካደሚክ ካውንስል ግምገማ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በማጠቃለያም በቅርቡ የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ለፀደቀላቸው ሶስት መምህራን እውቅና እና ሽልማት የተሰጠ ሲሆን፣ መድረኩን የአካዳሚክ ዘርፍ ዳይሬክተሮች፣ የሁሉም ኮሌጆችና ት/ቤቶች ዲኖች እና የት/ርት ክፍል ሀላፊዎች ተሳትፈውበታል።


የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.