የአፋርኛ ቋንቋ እና ስነ-ፅሁፍ የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የመመረቂያ ጥናታዊ ፅሁፍ አቀረቡ።

የአፋርኛ ቋንቋ እና ስነ-ፅሁፍ የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የመመረቂያ ጥናታዊ ፅሁፍ አቀረቡ።

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የአፋርኛ ቋንቋ እና ስነ-ፅሁፍ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የመመረቂያ ጥናታዊ ፅሁፋቸውን አቅርበዋል፡፡

ለቋንቋውም ሆነ ለሰመራ ዩኒቨርሲቲ  የመጀመሪያ የሆነው ይህ የድህረ-ምረቃ ፕሮግራም በመጀመሪያ ዙር በሁለት መስኮች  Applied linguistics and communication  እና Applied languistics and teaching ያስተማራቸው 11 ተማሪዎች ናቸው ጥናታቸውን ያቀረቡት።

የአፋርኛ ቋንቋ እና ስነ-ፅሁፍ ትምህርት ክፍል ከተከፈተበት 2006 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 11 አመታት በመጀመሪያ ዲግሪ በማስተማር በርካታ ምሁራንን ያፈራ ሲሆን ፣ የአፋርኛ ቋንቋ ካሪኩለሞችን ከመቅረፅ እና ከማስተማር ጀምሮ በስነ-ፅሁፍና በሚድያ ቋንቋው ይበልጥ እንዲበለፅግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡

መድረኩን የከፈቱት የአካደሚክ ጉዳዮች ም/ ፕሬዚዳንት ዶ.ር አብዱረህማን ከድር እንደገለፁት አንድን ቋንቋ ለማሳደግና ለማበልፀግ ከዚያም አልፎ የጥናትና የምርምር ቋንቋ እንዲሆን ማድረግ ለሁለንተናዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው:ዛሬ  የአፋርኛ ቋንቋ ከመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አልፎ የማስተርስ ጥናታዊ ፅሑፍ የሚቀርብት ቋንቋ መሆኑ አዲስ ታሪክ ያየንበት ቀን በመሆኑ እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል::

የመመረቂያ ጥናታዊ ፅሁፎቹን በመገምገሙ ረገድ የትምህርት ክፍሉ መምህራን፣ ከክልል የአፋርኛ ቋንቋ ማበልፀጊያ ማዕከል እንድሁም የግቢው ማህበረሰብ በተገኙበት ተከናውኗል።

=============

የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ

ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.