የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ተማሪዎች ስልጠና ተጠናቀቀ::

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ተማሪዎች ስልጠና ተጠናቀቀ::

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሰኔ 8/2016 ዓ.ም
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከኢፌዲሪ ሰላም ሚኒስቴር እና ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለሰመራ ዩኒቨርሲቲ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጭ ተማሪዎች “ብዝሃነት ለአብሮነት” በሚል መሪ ሀሳብ ከሰኔ 5-8/2016 ዓ.ም ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ::

በሰመራ ዩኒቨርሲቲ 300 የሚሆኑ ተማሪዎች የክረምት በጎ ፈቃድ ስልጠና የወሰዱ ሲሆን: በመጪው ወር ለሰመራ እና አካባቢው ማህበረሰብ ዘርፈ ብዙ በጎ ተግባራትን ለማከናወን ዝግጁ መሆናቸውን ሰልጣኞች ገልፀዋል:: አፈፃፀሙን በተመለከተ በማጠቃለያ ፕሮግራሙ ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል::

የክረምት ብሔራዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዋና አላማ ተሳታፊ ተማሪዎችን በዕውቀት፣ በአመለካከት እና በክህሎት እንዲበቁ በማድረግ ለሀገር ግንባታ፣ ብሄራዊ መግባባት፣ ለሁለንተናዊ ሰላምና ዘላቂ ልማት አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማድረግ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
#ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!


=================
✍️Public Relations Executive
Follow,Share and like our social media pages.
ፌስቡክ👇
https://www.facebook.com/susamara2008/
ቴሌግራም👇 https://t.me/SamaraUniversityEthiopia
ዩትዩብ👇 https://youtube.com/channel/UCvDWGawVYKQa_FJY8supkBA?sub_confirmation=1
ዌብሳይት👇
Www.su.edu.et
ትዊተር👇
https://twitter.com/SamaraunivEthio?t=QlDpWx8vlY_udWdGAztwvg&s=09
ሊንክድን👇
https://www.linkedin.com/company/semara-university/
ቲክቶክ👇
https://www.tiktok.com/@samara.university?_t=8ipUGAsrMwg&_r=1

Leave a Reply

Your email address will not be published.