የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ካውንስል በመውጫ ፈተና አፈፃፀም እና በ2016 የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የታቀዱ ተግባራት ላይ ተወያየ፡፡

የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ካውንስል በመውጫ ፈተና አፈፃፀም እና በ2016 የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የታቀዱ ተግባራት ላይ ተወያየ፡፡

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ካውንስል አባላት ተመራቂ ተማሪዎች በሚወስዱት የመውጫ ፈተና አፈፃፀም እና ውጤት ማሻሻል ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል፡፡

ለውይይቱ መነሻ እንዲሆን የ2015 ትምህርት ዘመን የመውጫ ፈተና አፈፃፀም፣ የተመዘገበው ውጤት ሪፖርት እና የ2016 በጀት አመት እቅድ በዩኒቨርሲቲው የፈተናዎች ማዕከል ዳይሬክቶሬት ቀርቧል፡፡

ባለፈው አመት ጥሩ ውጤት ቢመዘገብም ክፍተቶች እንደነበሩት የውይይት መድረኩን የከፈቱት የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዱረህማን ከድር አመላክተዋል፡፡

አያይዘውም ባለፈው አመት ለተመዘገበው ውጤት በዩኒቨርሲቲው የተሰሩ በርካታ ስራዎች እንዳሉ ሁኖ፡ በተለይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠ በመሆኑ በተግባራዊነቱ ላይ የነበረው መጠራጠር እና በሁሉም ወገን የነበረው የመሰረተ ልማት እና የስነ ልቦና ዝግጅት ማነስ እንደ ጉድለት የሚወሰዱ በመሆናቸው በቀጣይ ክፍተቶችን በማረም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችል አዲስ ሃሳብ እና አተገባበር ይዘው ወደ ስራ እንደሚገቡ ገልፀዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በዚህ ዓመት አጠቃላይ የምዝና ስራዎችን በማዘመን፣ የፈተናዎች ባንክ በማዘጋጀት እና ሌሎች አዳድስ አሰራሮችን በመቅረፅ እና በመተግበር ተማሪዎች ተቋሙን ከተቀላቀሉበት ዓመት ጀምረው በየኮርሶቹ የተቀመጡ ዝቅተኛ መስፈርቶችን ማሟላታቸውን በማረጋገጥ: ክፍተቶቻቸውን እየለዩ ለመስራት የሚያስችሉ አማራጮችን በመጠቀም የመውጫ ፈተናና የብቃት ምዘናን በአጥጋቢ ሁኔታ የሚያልፉ ተማሪዎችን ለማፍራት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ፣ እና ለዚህም ተግባራዊነት አስቻይ የግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ እንደሆነ አብራርተው ሁሉም የአካዳሚክ ካውንስል አባላት በንቃት እንድሳተፉ እና ወደ ተግባር በመለወጥ ውጤታማ ስራ እንድሰሩ አሳስበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.