የ USAID ከፍተኛ አመራሮች እና የቴክኒክ ቡድን በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ጉብኝት አደረጉ፡፡

የ USAID ከፍተኛ አመራሮች እና የቴክኒክ ቡድን በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ጉብኝት አደረጉ፡፡

የ USAID ከፍተኛ አመራሮች እና የቴክኒክ ቡድን አባላት በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው የስራ ውይይት እና ጉብኝት አድርገዋል፡፡

አመራሮቹ በዩኒቨርሲቲው የተገኙት ባለፈው ዓመት ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሞ በጋራ ሲሰራ በቆየው እና በ USAID የፋይናንስ ድጋፍ በሚደረግለት የከፍታ ፕሮጀክት አማካኝነት በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ለመምከር ነው፡፡

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት አብዱረህማን ከድር (ዶ/ር) አጠቃላይ ስለ ዩኒቨርሲቲው ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ከፍታ ፕሮጀክት (USAID Integrated Youth Activity) ከሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተቀጣሪነት ልማት እና ሙያ ዝግጁነት ማዕከል ጋር የተሠሩ ስራዎችን አስመልክቶ መምህር አይሸሽም ታደለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከፍታ ፕሮጀክት ከሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተቀጣሪነት ልማት እና ሙያ ዝግጁነት ማዕከል ጋር በመተባበር ባለፈው ዓመት ለተመራቂ ተማሪዎች የተለያዩ ስልጠናዎችን የሰጠ ሲሆን፣ለመምህራን ደግሞ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠቱ ተገልጿል፡፡
===========
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!

ማህበራዊ ገፆቻችንን ስለሚከታተሉ እናመሰግናለን!!!
Facebook 👇
https://www.facebook.com/susamara2008/
Telegram👇

https://t.me/SamaraUniversityEthiopia

You tube 👇

https://youtube.com/channel/UCvDWGawVYKQa_FJY8supkBA?sub_confirmation=1
Website 👇
Www.su.edu.et

Leave a Reply

Your email address will not be published.