የ2014/2015 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተጠናቀቀ

የ2014/2015 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተጠናቀቀ

የ2014/2015 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተጠናቀቀ።
==========================
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፡ ጥቅምት 11/2015 ዓ.ም

በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከመስከረም 30/2015 ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል የ2014/2015 የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ብሄራዊ ፈተና በሰላም ተጠናቋል።

ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያው ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 02/2015 እንድሁም በሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ከጥቅምት 08 እስከ 11/2015 ድረስ ሰላማዊ በሆነ መልኩ አስፈትኖ ወደየመጡበት እየሸኘ ነው።

ፈተናው ሰላማዊ ሁኖ እንድጠናቀቅ በትጋት የሰራችሁ ፈተና አስፈፃሚዎች፣ የፌደራል እና የክልል ፀጥታ አስከባሪዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ የፈተና ጣቢያ ሃላፊዎች፣ ፈታኞች፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ፣ የክልል፣ የዞን እና የወረዳ ትምህርት ቢሮ ሀላፊዎች ተወካዮች እና ተፈታኞች ላደረጋችሁት መልካም አስተዋፅኦ ዩኒቨርሲቲው ያመሰግናችኋል።

በዚህ ታሪካዊና ሀገራዊ የትምህርት ዘመቻ ላይ የተሳተፋችሁ የፈተና አስፈፃሚ እንግዶቻችን በሙሉ፣ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ እና በክልሉ በነበራችሁ ቆይታ የተገነዘባችሁትን መልካም ነገር ሁሉ ወደምትኖሩበት አካባቢ ስትመለሱ በማስተዋወቅ አንባሳደሮቻችን እንደምትሆኑ እናምናለን።

የሰላም አምባሳደር ወደሆነው ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በሰላም እንደመጣችሁና እንደቆያችሁ ሁሉ በሰላም ወደየአካባቢያችሁ እንድትደርሱ ዩኒቨርሲቲው ይመኛል።
==========================
ህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶት
ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.