የ2016 የእጩ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና(Exit-Exam) በሰላም ተጠናቋል።

የ2016 የእጩ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና(Exit-Exam) በሰላም ተጠናቋል።

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ: ሰኔ19/2016 ዓ.ም
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም የእጩ ተመራቂ የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና(Exit-Exam) ያለምንም ችግር አስፈትኖ በሰላም ተጠናቋል።

በዛሬው የመውጫ ፈተና ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ እና ህክምና ኮሌጅ 172 እንዲሁም ከግል የትምህርት ተቋማት 478 እጩ ተመራቂ የጤና ተማሪዎችን በተሳካ ሁኔታ አስፈትኗል::

ዩኒቨርሲቲው ራሱ ያሰለጠናቸውን(1427) ተማሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ የግል ኮሌጆችና የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡለትን ጨምሮ በድምሩ 2387 ተማሪዎችን መፈተኑን የፈተናዎች ማእከል መረጃ ያመለክታል።

ዩኒቨርሲቲው በሂደቱ የተሳተፉ የትምህርት እና የጤና ሚኒስቴር ተወካዮችን: የዩኒቨርሲቲውን ከፍተኛ አመራሮች : የፈተናዎች ማእከልን: የፈተና አስፈጻሚ ግብረ ሀይል አባላትን በሙሉ ለነበራችሁ ትጋትና የተናበበ አፈፃፀም ላቅ ያለ ምስጋናን ያቀርባል::

የዘንድሮው መውጫ ፈተና በ51 ማዕከላት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ3ኛ ጊዜ የተሰጠ ሲሆን: ይህም በት/ርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየተሰሩ ካሉ የለውጥ ስራዎች አንዱ ነዉ።

ዩኒቨርሲቲው ፈተናቸውን ላጠናቀቁ እጩ ተመራቂ ተማሪወች በሙሉ ከወድሁ እንኳን ደስ አላችሁ (Congratulations) ይላል፡፡
===========
#ማህበረሰቡን እናገለግላለን !!!
✍️የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ
==============
Follow,Share and like our social media pages.
ፌስቡክ👇
https://www.facebook.com/susamara2008/
ቴሌግራም👇 https://t.me/SamaraUniversityEthiopia
ዩትዩብ👇 https://youtube.com/channel/UCvDWGawVYKQa_FJY8supkBA?sub_confirmation=1
ዌብሳይት👇
Www.su.edu.et
ትዊተር👇
https://twitter.com/SamaraunivEthio?t=QlDpWx8vlY_udWdGAztwvg&s=09
ሊንክድን👇
https://www.linkedin.com/company/semara-university/
ቲክቶክ👇
https://www.tiktok.com/@samara.university?_t=8ipUGAsrMwg&_r=1

Leave a Reply

Your email address will not be published.