ዩኒቨርሲቲው ለክልሉ ማረሚያ ቤቶች ፖሊስ ኮሚሽን የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ዩኒቨርሲቲው ለክልሉ ማረሚያ ቤቶች ፖሊስ ኮሚሽን የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
==============
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ:የካቲት 11/2016 ዓ.ም
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ የመገልገያና የቢሮ ቁሳቁሶችን ለአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ፖሊስ ኮሚሽን ድጋፍ አድርጓል::
ከተሰጡት ንብረቶች ውስጥ ፍራሽ:ፋን:ወንበርና ጠረንጴዛ እንዲሁም ደስክቶፕ ኮምፒዩተሮች እንደሚገኙበት: እና በቀጣይ የሚደረጉ ድጋፎች እንዳሉ የዩኒቨርሲቲው የንብረት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ አህመድን አብዱሶመድ ገልጸዋል::
ስራ አስፈጻሚው በተጨማሪም በቅርቡ ለሠመራ ለጤና ሳይንስ ኮሌጅ 30 ጠረንጴዛ እና 50 ወንበሮችን ያስረከቡ መሆኑንና: ለአላሎበድ አስጎብኝዎች ማህበር ደግሞ 70 የጣሪያ ቆርቆሮ:ምስማር:የብረት በርሜሎችንና አልጋዎች:ችፑድ:የትራስና የአልጋ ልብሶችን ድጋፍ እንደተደረገ ገልጸዋል::
ንብረቶቹን ያስረከቡት የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተ/ም/ፕሬዝዳንት አቶ አደም አሊ፤ ሠመራ ዩኒቨርሲቲ “ማህበረሰቡን እናገለግላለን!” ብሎ ባስቀመጠው መሪ ቃል መሰረት የተማረ ዜጋን ከማፍራት በተጨማሪም በማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎቹ በየአመቱ በክልሉ ለሚገኙ የተለያዩ ተቋማት የሙያና የቁሳቁስ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል::
ድጋፉን የተረከቡት የማረሚያ ቤቶች ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አሀዱ መሀመድ ሀንፈሬ ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ጊዜያት በርካታ ድጋፎችን እንዳደረገላቸው ገልፀው: ፍሳሽ በማስወገድ እና የተለዩ መገልገያዎችን ድጋፍ ስላደረገልን እናመሰግናለን ብለዋል::
ዩኒቨርሲቲው ባለፈው አመት ካደረጋቸው ድጋፎች ውስጥ ለቲክኒክና ሙያ ኮሌጆች 1900 በላይ ወንበሮችና ጠረጼዛዎችን:ለአይሳኢታ መምህራን ኮሌጅ ከ450 ወንበርና ጠረንጴዛዎችን: ለአሚባራ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ወንበርና ጠረንጴዛ ድጋፍ ማድረጉ ከብዙው በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው::
================
ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!

የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ትስስር ገፆችን በመከተል: ትክክለኛ ተቋማዊ መረጃ ዎችን ይከታተሉ::
ፌስቡክ👇
https://www.facebook.com/susamara2008/
ቴሌግራም👇
https://t.me/SamaraUniversityEthiopia ዩትዩብ👇
https://youtube.com/channel/UCvDWGawVYKQa_FJY8supkBA?sub_confirmation=1
ዌብሳይት👇
Www.su.edu.et
ትዊተር👇
https://twitter.com/SamaraunivEthio?t=QlDpWx8vlY_udWdGAztwvg&s=09
ቲክቶክ👇
https://www.tiktok.com/@samara.university?_t=8ipUGAsrMwg&_r=1

Leave a Reply

Your email address will not be published.