ዩኒቨርሲቲው  ከአፋር ክልል እንስሳት ልማት ዘርፍ ቢሮ ጋር ስምምነት ተፈራረመ::

ዩኒቨርሲቲው ከአፋር ክልል እንስሳት ልማት ዘርፍ ቢሮ ጋር ስምምነት ተፈራረመ::

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከክልሉ የእንስሳት ልማት ዘርፍ በዋናነትም ከሰመራ እንስሳት ላብራቶሪ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል ::

የስምምነቱ አላማ ለእንስሳት ጤና ባለሙያዎች የትምህርት እድልና አጫጭር ስልጠናዎችን ማመቻቸት፣ የጋራ የምርምር ፕሮጀክቶችን መቅረፅ እና መስራት ፣ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን መስጠት ፣ የጋራ የህክምና እና ክትባት ዘመቻዎችን ማድረግ፣ የቤተሙከራ መሳሪያዎችን እና የህክምና ግብአቶችን በጋራ መጠቀም የሚያስችል ሁኔታን መፍጠር ነው ተብሏል።

የተቋማቱ በትብብር መስራት በዙሪያቸው ያለውን ሀብት፣ እውቀት እና አቅም አስተባብረው ማህበረሰቡን የጤናማ እንስሳት ሀብት ባለቤት እንዲሆን በማገዝ ፣ ኑሮው እንዲሻሻል እድል ከመፍጠሩ በላይ፣ለክልሉ እና ለሀገር ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ ያበረክታል ሲሉ የሁለቱም ተቋማት አመራሮች ተናግረዋል፡፡

የሁለቱም ተቋማት ባለሙያዎች የጋራ እቅድ በማቀድ በዘርፉ የተሰማሩ አጋር አካላትን በማስተባበር የእንስሳት ጤና ጥበቃን በማህበረሰብ አገልግሎት ስራ ተደራሽ  ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ሁለቱም ወገኖች ገልፀዋል።

ስምምነቱን የፈረሙት የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብዱረህማን ከድር እና  የክልሉ የእንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሂም መሀመድ ናቸው::

============

ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!

የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ

Leave a Reply

Your email address will not be published.