ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የምርምር ዉጤቶችን ላሳተሙ ተመራማሪዎች ሽልማት ሰጠ::

ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የምርምር ዉጤቶችን ላሳተሙ ተመራማሪዎች ሽልማት ሰጠ::


#ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሰኔ 13/2016ዓ.ም
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በታወቁ አለምአቀፍ ጆርናሎች ላይ ከፍተኛ የምርምር ዉጤቶችን ላሳተሙ ከ1ኛ እስከ 5ኛ ደረጃ ለያዙት ተመራማሪዎች የSumsung A54 smart phone ሽልማትና ሰርተፊኬት ሰጥቷል፡፡

በዚሁ መሰረት፣ ኩሴ ኡርማሌ፣በእምነት ለማ ፣ ተመስገን ገበየሁ ፣ እፀይ ወልዱ እና ከበደ ገመዳ በቅደም ተከተል ከ1-5 ደረጃን የያዙ ተመራማሪዎች ሲሆኑ ሽልማታቸውን ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን እጅ ተቀብለዋል።

በተጨማሪም ከ6ኛ-10ኛ ደረጃ ለያዙት ተመራማሪዎች ሰርተፊኬት እንደሚሰጥ ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል፡፡

መሰል የምርምር ስራዎች መብዛታቸው ለሌሎች ተመራማሪወች ፣ ለመምህራን ፣ ለተማሪዎች እንድሁም ለማህበረሰቡ የሚሰጠው ጥቅም ብዙ ከመሆኑም በላይ የትምህርት ጥራትን እና የምርምር ባህልን ለማሳደግ እንደሚያስችልም በሽልማቱ ወቅት ተነስቷል፡፡

ዶ/ር መሀመድ ግንቦት 05/2014 ዓ.ም ከመምህራን ጋር ባደረጉት ውይይት የምርምር ውጤት በብዛት የሚያሳትሙ ምሁራንን ለመሸለም ቃል መግባታቸውን ዘግበን የነበረ ሲሆን ፣ በዚሁ መሰረት ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ተከናውኗል ::

የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚደንት ፅ/ቤት ፣ የምርምር ፣ ህትመት ፣ ስነ ምግባርና ስርፀት ዳይሬክቶሬት ሂደቱን በማስቀጠል ትልቅ ሚና የነበረው ሲሆን ለቀጣይ ስራዎችም ጭምር የሚያበረታታ መሆኑ ተገልጿል::

ዩኒቨርሲቲው ለተሸላሚዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ያስተላልፋል፡፡
#ማህበረሰቡን እናገለግላለን
✍️የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ

 


Follow,Share and like our social media pages.
ፌስቡክ👇
https://www.facebook.com/susamara2008/
ቴሌግራም👇 https://t.me/SamaraUniversityEthiopia
ዩትዩብ👇 https://youtube.com/channel/UCvDWGawVYKQa_FJY8supkBA?sub_confirmation=1
ዌብሳይት👇
Www.su.edu.et
ትዊተር👇
https://twitter.com/SamaraunivEthio?t=QlDpWx8vlY_udWdGAztwvg&s=09
ሊንክድን👇
https://www.linkedin.com/company/semara-university/
ቲክቶክ👇
https://www.tiktok.com/@samara.university?_t=8ipUGAsrMwg&_r=1

Leave a Reply

Your email address will not be published.