ዩኒቨርሲቲው ከ STEM POWER ጋር በመተባበር በComputer stream እና Electronics stream ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ::

ዩኒቨርሲቲው ከ STEM POWER ጋር በመተባበር በComputer stream እና Electronics stream ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ::
================
በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ከ STEM POWER ጋር በመተባበር በComputer stream እና Electronics steam ላይ ያተኮረ የአሰልጣኞች ስልጠና ከየካቲት 06-08 /2016 ዓ.ም ተሰጥቷል።
ስልጠናውን የሰጡት ከSTEM POWER የመጡ ባለሞያዎች ሲሆኑ: ከፊዚክስ፣ ኤሌክትሪካልና ኮምፒውተር ምህንድስና፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፣ ኮምፒውተር ሳይንስ ት/ርት ክፍሎች የተውጣጡ 25 መምህራን ስልጠናውን እንደወሰዱ አስተባባሪው የኢንዱስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ገልጿል።
ስልጠናዉ ነጥቦች በ Computer stream-ዘርፍ Virtual computer installations and configuration, Introduction to Solar Energy & 3D printer operation እንዲሁም በ Electronics Stream- ዘርፍ Virtual Computer Installations and Configuration, Introduction to Solar Energy & Fundamental of Electronics ዙሪያ የተሰጠ የአሰልጣኞች ስልጠና መሆኑ ተመላክቷል::
በዚህም ዩኒቨርሲቲው የSTEM መምህራኖችን አቅም በመገንባት ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከተለያዩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በርካታ ተማሪዎችን እየመለመለ ስልጠና እየሰጠበት ያለውን የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ ማእከል (STEM) ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚረዳም ተገልጿል፡፡
የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው
በ8ኛው ሀገር አቀፍ የሳይንስና ኢንጂነሪንግ ውድድር (8th annual National Science and Engineering Fair) ላይ የሰሩትን “Flood Alert system” የፈጠራ ስራ አቅርበው ተሸላሚ መሆናቸው የሚታወስ ነው::
================
ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!
የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ
በማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን የሚወጡ ትክክለኛ መረጃዎችን ለመከታተል::
ፌስቡክ👇
ዌብሳይት👇
ትዊተር👇
ቲክቶክ👇

Leave a Reply

Your email address will not be published.