ዩኒቨርሲቲው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች እንዲሁም ፈተና ለሚያስፈፅሙ ሱፕርቫይዘሮች እና ፈታኝ መምህራን ኦረንቴሽን ተሰጠ።

ዩኒቨርሲቲው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች እንዲሁም ፈተና ለሚያስፈፅሙ ሱፕርቫይዘሮች እና ፈታኝ መምህራን ኦረንቴሽን ተሰጠ።

ዩኒቨርሲቲው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ።
#ሰመራዩኒቨርሲቲ_ሀምሌ_02_2016ዓ.ም
የ2016 የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች አጠቃላይ የፈተናውን አሰጣጥ የተመለከተ ኦረንቴሽን ተሰጥቷል።

በኦረንቴሽኑ የተፈታኞችን መብትና ግዴታዎች:አጠቃላይ የፈተና ሂደቱን ጨምሮ የስነ ልቦና ጥንካሬን የሚሰጡ ምክሮች ከአመራሮቹ ተሰጥተዋል::

በኦረንቴሽኑ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን፣ የትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱ ሃሰን፣ ኮሚሽነር ባሱ ኢሴ: የትምህርት ሚኒስተር ተወካይ : የፈተና ጣቢያ ሃላፊዎች እና ሌሎች አስፈፃሚ አካላት ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

ዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የሆነ የፈተና ሂደት እንዲኖር መመሪያው የሚፈቅድለትን ሁሉ እንደሚያደርግ የገለፀ ሲሆን ሁሉም አስፈጻሚ አካላት እንዲሁም ተፈታኞች በላቀ ስነምግባር ፈተናውን እንድወስዱ መልዕክት ተላልፏል::

=======================

በዩኒቨርሲቲው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚያስፈፅሙ ሱፕርቫይዘሮች እና ፈታኝ መምህራን ኦረንቴሽን ተሰጠ።
#ሰመራዩኒቨርሲቲ_ሀምሌ_02_2016ዓ.ም

የ2016 የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለማስፈፀም ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ ፈታኝ መምህራን እና የፈተና አስፈፀሚ አካላት አጠቃላይ የፈተናውን አሰጣጥ የተመለከተ ኦረንቴሽን ተሰጥቷል።

ኦረንቴሽኑን የሰጡት ከትምህርት ሚኒስተር የተወከሉ የፈተና ሃላፊ እና አስተባባሪ ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው ለአስፈፃሚ አካላት፣ ለፈታኝ መምህራን፣ ለፀጥታ አካላት እና ለተፈታኞች ምቹ እና ሰላማዊ ሁኔታን ለመፍጠር መመሪያ እና አቅሙ የሚፈቅድለትን ሁሉ እንደሚያደርግ በዩኒቨርሲቲው በኩል ተገልጿል።
=====================

#ማህበረሰቡንእናገለግላለን!!
✍️የህዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ
For More, Visit,Follow,Share and like our social media pages.
ፌስቡክ👇
https://www.facebook.com/susamara2008/
ቴሌግራም👇
https://t.me/SamaraUniversityEthiopia 
ዩትዩብ👇
https://youtube.com/channel/UCvDWGawVYKQa_FJY8supkBA?sub_confirmation=1
ዌብሳይት👇
Www.su.edu.et

Leave a Reply

Your email address will not be published.