ዩኒቨርሲቲው 18ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በደማቅ ሁኔታ አከበረ::

ዩኒቨርሲቲው 18ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በደማቅ ሁኔታ አከበረ::

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ, ህዳር 25, 2016 ዓ.ም
“ብዝሓነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነታችን” በሚል መሪ ቃል:በጠዋት እና ከሰአት በሁለት መርሃ-ግብሮች በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል፡፡
በጠዋቱ መርሃ-ግብሮች ችግኞችን የመንከባከብ ስራ የተሰራ ሲሆን ሁሉም ም/ፕሬዚዳቶች የካውንስል አባላት እና የተማሪ ተወካዮች የተሳተፉበት ሲሆን ከሰአት በኃላ
የፓናል ውይይት፣ የባህል ትርኢት እና የሥነ-ጽሁፍ ዝግጅቶች የቡበት ሆኖ ተከብሯል::
በፓናል ውይይቱ መክፈቻ የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር ሁሴን ኡመር እንደተናገሩት፤የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዩኒቨርሲቲያችን መከበሩ: በተማሪዎች እና ሰራተኞች መካከል ይበልጥ ብዝሀነትን እና እኩልነትን በማሳየት መከባበርንና የላቀ ማህበራዊ ተግባቦትን ይፈጥራል ብለዋል::

የፓናል ውይይቱን የተማሪዎች ድን ፅ/ቤት ሀላፊ አብዱ ሀንፈሬ የመሩት ሲሆን: መምህር አብራሀ አረፋይኔ ጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች:ዳይሬክተሮች: ስራ አስፈጻሚዎች:ቡድን መሪወች:የተማሪ ህብረት:የሰላም ፎረም አባላት እና ተማሪወች ተገኝተውበታል::
18ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን “ብዝሃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል ህዳር 29 በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማ ይከበራል።ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!
የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ

Leave a Reply

Your email address will not be published.