ዳሎል የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ለሀገር ግንባታ ተመሰረተ።

ዳሎል የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ለሀገር ግንባታ ተመሰረተ።

ዳሎል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ለሀገር ግንባታ በአራት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማለትም በሰመራ፣ ወልድያ፣ ወሎ እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ በመሆን የመሰረቱት ነው::

ፎረሙ በቀጣይ ሁሉንም ዩኒቨርሲቲዎች በማቀፍ እውቀትንና ሀብትን በማስተባበር ለሀገር ግንባታ ግብአት የሚሆኑ የምክክር መድረኮችን:ጥናትና ምርምሮችን እንዲሁም  ሀገራዊ  ዕሴቶችን በማስተማር የትምህርት ተቋማት ለሀገር ግንባታ የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ የሚያስተባብር ነው ተብሏል::

ፎረሙ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መሀመድ ኡስማን (ዶ/ር) ሰብሳቢ አድርጎ የመረጠ ሲሆን የአራቱን ዩዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች መስራች ኮሚቴ እንዲሁም ከየዩኒቨርሲቲወቹ የተውጣጡ አራት ምሁራንን የቴክኒክ ኮሚቴ አድርጎ መርጧል። 

ምስረታው የተከናወነው ሰመራ ዩኒቨርሲቲ  ”ለሀገራዊ ማንነትና እሴት ግንባታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና ” በሚል ርዕስ ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ወቅት ሲሆን: የተከበሩ አቶ ታየ ደንደኣ የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስተር ዲኤታ እና የዩኒቨርሲቲዎቹ ፕሬዚዳንቶችና ተወካዮች: የአንትሮፖሎጂ መምህር እና ተመራማሪው ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ በተገኙበት መድረክ ነው::

==============

የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.