የአፋርኛ ቋንቋ መምህራንን የምርምር መስራት አቅም ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና እየተሰጠ ነው

የአፋርኛ ቋንቋ መምህራንን የምርምር መስራት አቅም ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና እየተሰጠ ነው


=======================================================================

የአፋርኛ ቋንቋ መምህራንን የምርምር መስራት አቅም ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
=======================================================================
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፡ ህዳር 12/2015 ዓ.ም
ትኩረቱን በአጠቃላይ የቋንቋ ጥናትና ምርምር(research)፣ የአፋርኛ ቋንቋ ዘየ(Afar language Dialects)፣ቃላዊ ቋንቋ(oral tradition) እና ሳይንሳዊ ጥናታዊ ፅሁፍ ዝግጂትን (Article writing) ጨምሮ የመምህራንን ምርምር የመስራት አቅም ሊያሳድግ የሚችል ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው፡፡

ስልጠናውን የሚሰጡት የጅቡቲ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶ/ር መሀመድ ሃሰን ካሚል ሲሆኑ፣ ሰልጣኞቹ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የአፋርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል መምህራን እና የሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎች ሲሆኑ፣ ለአራት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ስልጠናውን ያስጀመሩት የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ቤተልሄም ዳኘው “ስልጠናው አፋርኛ ቋንቋን የምርምር ቋንቋ ለማድረግ የተያዘውን እቅድ እውን ለማድረግ አንድ እርምጃ መሆኑን ገልፀው በቅርቡ ዩኒቨርሲቲው ለሚከፍተው የአፋር ባህል እና ቅርስ ጥናት ማእከል ስራ መሳለጥ ትልቁን ሚና የሚወጣ ምሁራን ለመፍጠር ትልቅ ትርጉም እንደሚኖረው አብራርተዋል፡፡

ም/ፕሬዝዳንቷ አያይዘውም ስልጠናው ሲዘጋጅ ዩኒቨርሲቲው በያዘው የቱሪዝም የልህቀት መስክ በተገቢው ልክ ልቆ ለመገኘት በቋንቋው ሰፊ ጥናት ለመስራት በማለም ስለሆነ ስልጠናውን በሃላፊነት እና ትርጉም ያለው የማህበረሰብ አግልግሎት ስራን ለመስራት እድሉን ያገኛችሁ መሆኑን በመገንዘብ በትኩረት በመከታተል ሀላፊነታችሁን እንድትወጡ ሲሉ ሰልጣኞችን አሳስበዋል፡፡
=======================================================================
ህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶት
ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.