ዩኒቨርሲቲው “Transition Roadmap towards a University of Applied Sciences” በሚል ርዕስ ወርክሾፕ አካሄደ።

ዩኒቨርሲቲው “Transition Roadmap towards a University of Applied Sciences” በሚል ርዕስ ወርክሾፕ አካሄደ።
==========
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ፤ የካቲት 04/2016 ዓ.ም
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ወደ ተግባር ዩኒቨርሲቲነት ለመሸጋገር የሚመራበት ፍኖተ ካርታ (Roadmap) የመጀመሪያ ረቂቅ መጠናቀቁን አስመልክቶ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ ግብዓት ለመሰብሰብ እና ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ወርክሾፕ አካሂዷል።
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዱረህማን ከድር እንደገለፁት “በሀገራችን የተጀመረው የትምህርት ፍኖተ ካርታ የፖሊሲ ለውጥን መነሻ በማድረግ እና ከትምህርት ጥራትና ፍትሃዊ ተደራሽነት አንፃር እንደ ሀገር የተግባባንበትን ነጥብ ይዘን ጊዜውን የሚመጥን ተግባር ተኮር ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ግልፅ ፍኖተ ካርታ እንዲሆን በጥልቀት መገምገም እና ጥሩ ግብዓት ማበርከት አለብን” ብለዋል።
በመድረኩ ከተለያዩ አለም አቀፍ የትምህርት ተቋማት የተቀሰሙ ተሞክሮዎች በመነሳት የተዘጋጀው የዩኒቨርሲቲው የአፕላይድ ሳይንስ ሽግግር ፍኖተ ካርታ ፣ የተቋሙን አሁናዊ ሁኔታ በግልፅ ከሚያሳዩ መረጃዎች ጋር ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀውን ፍኖተ ካርታ አፅድቆ የተጀመሩ የሽግግር ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል በተግባር የታገዘ ትምህርት በመስጠት:የምርምር ስራወችን ወደ ማህበረሰብ በማውረድ ለአካባቢው ብሎም ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት የበኩሉን አስተዋጽዖ ማበርከት እንዳለበት በመድረኩ ተነስቷል።
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሰረት
የተግባር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ (University of Applied Sciences) ምድብ ውስጥ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ትኩረት አድርጎ የሚሰራባቸው መስኮች (excellence areas) ደግሞ ግብርና: ማእድን እና ቱሪዝም ናቸው::
በፕሮግራሙ ላይ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የምርምርና አካዳሚክ ደይሬክተሮች ፣ ኮሌጅ ዲኖች፣ ም/ድኖች፣ የት/ርት ክፍል ኃላፊዎች፣ ሲኒየር መምህራን ተሳትፈዋል ።
Facebook 👇

Leave a Reply

Your email address will not be published.