በዩኒቨርሲቲው የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተና ተጀመረ::
#ሰመራዩኒቨርሲቲ_ሀምሌ_03_2016ዓ.ም
የ2016 ዓ.ም የመጀመርያው ዙር የ12ኛ ክፍል ማህበራዊ ሣይንስ ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ብሄራዊ ፈተና ተጀምሯል።

ፈተናውን የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን እና የአፋር ክልል የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱ ሀሰን: የትምህርት ሚኒስተር ተወካይ : የፈተና ጣቢያ ሃላፊዎች እና ሌሎች አስፈፃሚ አካላት በተገኙበት አስጀምረውታል።

በ2016ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ለመፈተን በዩኒቨርሲቲው የተመደቡ 5ሺ 46 ተማሪዎች ሲሆኑ በአሁኑ የመጀመርያው ዙር 2ሺ 301 የማህበራዊ ሣይንስ ተማሪዎች ዛሬ መፈተን ጀምረዋል::

ዩኒቨርሲቲው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናውን በወረቀት እና በኦንላይን እየሰጠ እንደሚገኝም ተመላክቷል::

በሁለተኛው ዙር 2ሺ 745 የተፈጥሮ ሣይንስ ተማሪዎች እንደሚፈተኑ ይጠበቃል::

በዩኒቨርሲቲው የሚሰጠው ብሄራዊ ፈተና ሰላማዊ ሆኖ እንድጠናቀቅ እና ለተፈታኞች ጥሩ ውጤት እንድመጣላቸው ዩኒቨርሲቲው ምኞቱን ይገልፃል።
#ማህበረሰቡንእናገለግላለን!!
✍️የህዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ
For More, Visit,Follow,Share and like our social media pages.
ፌስቡክ👇
https://www.facebook.com/susamara2008/
ቴሌግራም👇
https://t.me/SamaraUniversityEthiopia
ዩትዩብ👇
https://youtube.com/channel/UCvDWGawVYKQa_FJY8supkBA?sub_confirmation=1
ዌብሳይት👇
Www.su.edu.et

Leave a Reply

Your email address will not be published.