32ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል

32ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል

 

32ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል።

ህዳር 19/2016 ዓ.ም

32ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ “የትምህርት ጥራት ለሁለንተናዊ እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ በጅግጅጋ ተካሂዷል።።

ላለፉት ሶስት ቀናት በተካሄደው ጉባኤ የትምህርት ዘርፍ ሪፎርም ስራዎች አፈጻጸም ሪፖርት፣ የ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት ያጋጠሙ ችግሮችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ፣ የመውጫ ፈተና አፈጻጸምና ቀጣይ አቅጣጫዎች፣ የመምህራንና አመራር አቅም ግንባታ ንድፈ- ሃሳብ ሰነድ፣ የመረጃ ስርዓት ተግዳሮትና ተዓማኒነት ላይ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዷል።

ጉባኤው ውጤታማ ተግባራትን በማስቀጠል በዘርፉ የተጋረጡ ተግዳሮቶች ላይ በመወያየት የጋራ መፍትሄ ለማስቀመጥ ያግዛል ተብሏል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በትምህርት ዘርፍ የሚደረገው የማሻሻያ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው: ይህም ብቁ ዜጎችን ለመፍጠር ዕድል የሚሰጥ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

በጉባኤው ላይ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ፣ የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች እና ም/ፕሬዚዳንቶች፣ የክልል የትምህርት ዘርፍ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል።

ምንጭ:- ትምህርት ሚኒስቴር፣ኢዜአ፣ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.