Start
End
በሰኔ ወር መገባደጃ ላይ የተጀመረው የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር፣ ለሁለተኛው ዙር ተከላ ከሐምሌ 10 እስከ 20/2014 ዓ.ም ለአስር ቀናት ሲከናወን ቆይቶ ዛሬ ተጠናቋል፡፡
በግብርና ኮሌጅ አስተባባሪነት በዚህ ዙር በአጠቃላይ ወደ 5ሺ የሚጠጉ ችግኞች ለመትከል መታቀዱን የገለፁት የግብርና ኮሌጅ ዲን የሆኑት መምህርት ሰአዳ አህመድ ተከላው በሚወጣው መርሃ-ግብር መሰረት የዳይሬክቶሬት ጽ/ቤቶች፣ ኮሌጆች እና ት/ቤቶች በመከፋፈል እንደሚያከናውኑት አመላክተዋል፡፡