የMakerspace አለም አቀፍ አውደ ጥናት በስኬት ተጠናቀቀ::

የMakerspace አለም አቀፍ አውደ ጥናት በስኬት ተጠናቀቀ::

ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ:ህዳር 12፣ 2017ዓ.ም
በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ቀናት ከአፍሪካ እና አውሮፖ 9 ዩኒቨርሲቲዎችን በማሳተፍ የተካሄደው የኢትዮጵያ-ጅቡቲ ሴቶች EtD-FaM Makerspace አለም አቀፍ አውደ ጥናት በስኬት ተጠናቋል::

EtD-FaM Makerspace ፕሮጀክት ሴቶች የሙያ ስራ ሊማሩበት እና ሊሰሩበት የሚችሉበትን የመስሪያ ቦታዎች በተግባር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ማቋቋም እና ማጎልበት ሲሆን: ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ያሉ አስተማሪዎች፣ ተመራማሪዎች እና መካከለኛና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች መካከል ትስስርን ለመፍጠር ያለመ ነው።

በአውደ ጥናት መክፈቻ እና መዝጊ ላይ ንግግር ያደረጉት የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን ፕሮጀክቱን ወደ አፕላይድ ሳይንስ በሽግግር ላይ ላሉ ዩኒቨርሲቲዎች በትክክለኛው ጊዜ የመጣ እውቀትን ከሚሰሩ እጆች ጋር የሚያገናኝ ሲሉ ገልጸውታል።

አውደ ጥናቱ “Empowering Hands, Empowering Minds” በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደ ሲሆን በታወቁ የውጪ እና የሀገር ውስጥ ምሁራን 15 ጥናታዊ ፅሁፎች የቀረቡበት እና Makerspace ልምድ ያካበቱ የዘርፉ ምሁራን የተመራ ተከታታይ ግንዛቤ ያላቸው ገለጻዎችና ውይይቶች ቀርበውበታል።

በዚህ አውደ ጥናት በፕሮጀክቱ የታቀፉ 5 ዩኒቨርሲቲዎች (ሰመራ፣ ድሬዳዋ፣ ወሎ፣ አርሲ እና ወለጋ) ተወካዮች ከሀገር ውስጥ እና ከአለም አቀፍ የጅቡቲ፣የጣሊያ፣ የጀርመን እና ኦስትሪያ ዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮች:እንዲሁም ከትምህርት ሚኒስቴር ዶ/ር ኤባ ሚጄና እና ዶ/ር ሰራዊት: የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፈቃዱ ምትኩን ጨምሮ የፕሮጀክቱ አስተባባሪና ገምጋሚዎች ፕ/ር ዶ/ር-ኢንግ ቶማስ ቤንዝ: ዶ/ር ማርጋሬት ግፍሬር: ዶ/ር ማርዋ ቤን አሊ:ዶ/አሚና እና ተጋባዥ ባለ ድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል::

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ወደ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲነት ለጀመረው ሽግግር የተዘጋጀ ፍኖተ ካርታ በአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ ፕሬዝዳንቱ ዶ/ር አብዱረህማን ከድር የቀረበ ሲሆን ለሌሎች የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች ተሞክሮው ይጠቅም ዘንድ በመፅሐፍ ታትሞ ለተሳታፊውች ተሰጥቷል።

ይህ አውደ ጥናት ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የጀመረውን የአለም አቀፋዊነት ጥረት ይበልጥ ያጠናከረ ከመሆኑም በላይ ከሀገር ውስጥ:እና ከሁለት አህጉር (ከአፍሪካ እና አውሮፓ) የትምህርት ተቋማት ጋር ለመተባበር እና እውቀትን ለመጋራት ተጨማሪ እድል የሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

በመጨረሻም ለጥናት አቅራቢ ምሁራን የምስክር ወረቀት እና ለውጪ እንግዶች የባህል ትውውቅን የሚገልፁ ባህላዊ አልባሳትን በመስጠት ተጠናቋል::

ማህበረሰቡን_እናገለግላለን!!!
✍️የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *