በዩኒቨርሲቲው የኤች.አይ.ቪ ኤድስ: አካል ጉዳተኞች እና የነጭ ሪቫን ቀን ተከብሯል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የኤች.አይ.ቪ ኤድስ: አካል ጉዳተኞች እና የነጭ ሪቫን ቀን ተከብሯል፡፡

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ :ህዳር 21/2017ዓ.ም

በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ: አካል ጉዳተኞች እና የነጭ ሪቫን ቀን አንድ ላይ በልዩ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብረው ውለዋል፡፡

የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ37ኛ፣ በኢትዮጵያ ለ36ኛ ጊዜ”ሰብአዊ መብትን ያከበረ የኤች አይ ቪ አገልግሎት ለሁሉም!” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል::

የአካል ጉዳተኞች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ32ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል::

የነጭ-ሪቫን ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ16 ኛ ጊዜ የሚከበር ነው::

የዛሬውን መድረክ የዩኒቨርሲቲው የሴቶች እና ማህበራዊ አካቶ ሥራ አስፈጻሚ ከአፋ/ብ/ክ/መ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ጋር በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን በመድረኩ ኤች.አይ.ቪ ኤድስ በሀገራችን የተዘነጋ የሚመስል ነገር ግን በጣም እየተስፋፋ እንደሆነ በመጥቀስ የወረርሽኙን ስርጭትን ለመግታትና ለመቆጣጠር ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

እንዲሁም የአካል ጉዳተኛ ወገኖችን እኩል ተጠቃሚነት እና የአካል ጉዳትን ያገናዘበ አገልግሎት እንዲኖር ለማስቻል የሁሉምን ጥረት እንደሚሻ ተገልጿል፡፡

ነጭ ሪባን ቀን በሴቶች ላይ የሚፈጸም ብዙ መልክ ያለው ሕገ ወጥ ድርጊት/ጥቃት ሲሆን ሴት ሕፃናትና እናቶች በጾታቸው ምክንያት አካላዊ፣ ሥነ ልቦናዊ፣ ወሲባዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቃቶች የሚደርስባቸው በተዛባ አመለካከት በመሆኑ ጥቃቶችን ለማስቆም ሁሉም ይመለከተኛል ብሎ መታገል እንደሚገባው በውይይት መድረኩ ተነስቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *