በእንስሳት ጤና እና ደህንነት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ተከናወነ።

በእንስሳት ጤና እና ደህንነት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ተከናወነ።

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ታህሳስ_23/2017 ዓ.ም

የሠመራ ዩኒቨርሲቲ እንስሳት ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ከኢትዮጵያየእንስሳት ሀኪሞች ማህበር Ethiopian Veterinary Association (EVA) እና Society for the Protection of Animals Abroad (SPANA) ከተባሉ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የእንስሳት ጤና እና ደህንነት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እንዲሁም የህክምና አገልግሎት በሎጊያ እና ዱብቲ አካባቢዎች ተሰጥቷል።

የእንስሳት ጤና ትምህርቱን ከEVA እና SPANA የመጡ ባለሙያዎች ከዩኒቨርሲቲው የእንስሳት ህክምና መምህራን እና የአንድ ጤና ክለብ ተማሪዎች በጋራ አከናውነውታል።

በቀጣይም ሶስቱ ተቋማት በእንስሳት እና ማህበረሰብ ጤና ላይ በቅንጂት ስራዎችን እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *