የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል ተጀመረ

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል ተጀመረ

ሰመራዩኒቨርሲቲጥር 17/2017 ዓ.ም

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ከጥር 17-27 /2017 ዓ.ም በሚካሄደው የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል ላይ በ3 የስፖርት አይነቶች፣ የወንዶች አትሌቲክስ በሁሉም አይነት፣ ቴኳንዶ በሴት እና ወንድ እንዲሁም በእግር ኳስ እንደሚወዳደር መረጃውን ያደረሱን የአስተዳደር እና ልማት ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር ሁሴን ኡመር ናቸው።

ለሰባት አመታት ተቋርጦ የነበረው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ(ፕ/ር) በተገኙበት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሯል፡፡

በአምስት የስፖርት አይነት ከ 49 የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ ተማሪዎች የሚሳተፉበት ይህ ውድድር በደማቅ ባህላዊ ትርዒት ታጅቦ ተከፍቷል።

ለሰመራ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ልኡክ መልካም እድል እንመኛለን!!

✍️ Public Relations Executive.
For further updates, please follow our social media channels.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *