
የራያ ዩኒቨርሲቲ በርዕደ መሬት ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ የአዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳ ነዋሪዎች ድጋፍ አደረገ::
ሰመራዩኒቨርሲቲጥር 21/ 2017 ዓ.ም
የራያ ዩኒቨርሲቲ በርዕደ መሬት ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ የገቢ ረሱ ዞን አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳ ነዋሪዎች ድጋፍ አደረገ::

የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጄኔ ድጋፉን ካስተባበሩት የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ.ር መሀመድ ኡስማን ጋር በመሆን በመጠለያ ጣቢያው በመገኘት የአፋ/ብ/ክ/መ ላቋቋመው ድጋፍ አሰባሳቢግብረሃይ አስረክበዋል::
የግብአት አቅርቦቱ ለወገን የእለት ጉርስ ከማድረስ ባለፈ የማህበረሰብ ትብብርን እና አብሮነትን በተግባር ለመግለፅ እና ለሌሎችም አርአያ እንዲሆን በማሰብ የተደረገ ነው ሲሉ ፕሮፌሰር ታደሰ ገልፀዋል::
ከመስከረም ጀምሮ በተደጋጋሚ በተከሰተው ርዕደ መሬት ምክንያት በገቢ ረሱ ዞን አዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ካሉ 6 ቀበሌዎች 10ሺ የሚሆኑ ነዋሪዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው በ 3 መጠለያ ጣቢያዎች እንደሚገኙ እና ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ እንዲሁም ወደተሻለ ቦታ ለማዘዋወር እየተሰራ እንደሆነ የአደጋና ስጋት መከላከል ቢሮ ም/ሀላፊ በርክክቡ ወቅት ገልጾልናል::

በርክክቡ ወቅት የራያ እና የሰመራ ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች: የገቢ ረሱ ዞን አመራሮች:የአደጋና ስጋት መከላከል ቢሮ አመራሮች እንዲሁም የማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል::
ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ የምርምር እና የማህበረሰብ ተኮር ፕሮጀክቶችን እየሰሩ እንደሚገኙም ተገልጿል።
📸 ✍️መ/ድ አ/ድ አበጋር
We serve the community!
✍️ Public Relations Executive