ዩኒቨርሲቲው የግማሽ አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ አካሔደ።

ዩኒቨርሲቲው የግማሽ አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ አካሔደ።

ሰመራዩኒቨርሲቲ፤ጥር 21/2017 ዓ.ም-ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ.ም የግማሽ አመት (የ6 ወር) የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለካውንስል አባላት ቀርቦ ገንቢ የሆነ ግምገማ እና ውይይት ተደርጓል።

የየግማሽ አመት የስራ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ወቅቱን የጠበቀ እና የአፈጻፀሙን ጥንካሬና ድክመት ለመለየት የሚያስችል ግምገማ በማድረግ በሁሉም የሥራ ክፍሎች ውስጥ ትኩረት የሚሹ ተግባራትን በመንቀስ በውይይት የበለፀገ ሪፖርት ለማዘጋጀት የሚያግዝ ግብአት የተገኘበት ነው ሲሉ መድረኩን የመሩት የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚደንቱ ሁሴን ኡመር (ዶ/ር) ገልጸዋል ።

አያይዘውም በዩኒቨርሲቲው ሁሉም የሥራ ክፍሎች የቁልፍ አመላካቾች(KPI) ከከፍተኛ አመራር እስከ ግለሰብ ፈፃሚ ድረስ ተፈራርመን በማውረድ ወደ ስራ ስለገባን በቀጣይ ስድስት ወራት የሚሰሩ ስራዎች እና የአፈጻጸም ሪፖርታችን በገባነው ስምምነት መሰረት እንደሚቃኝ በቂ ግንዛቤ የፈጠረ መድረክ መሆኑንም አስረድተዋል።

የአፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረቡት የስትራቴጅክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንድሪስ ሰይድ ሲሆኑ: ከተሳታፊዎች በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስዋል: ከመድረክ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው ውይይቱ ተጠናቋል።

ማህበረሰቡንእናገለግላለን!!!

✍️የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *