የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ከመካከለኛ አመራሮች ጋር በቁልፍ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ::

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ከመካከለኛ አመራሮች ጋር በቁልፍ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ::

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_መጋቢት_25/2017 ዓ.ም

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን በቁልፍ የአፈፃፀም ጉዳዮች ፣በመውጫ ፈተና ፣ የሰራተኞች የብቃት ምዘና እና ከመሀል ሆኖ መምራት ላይ ያተኮረ ውይይት ከመካከለኛ አመራሮች ጋር አድርገዋል::

ፕሬዚዳንቱ በመሩት በዚህ መድረክ ለውይይት መነሻ የሚሆኑ በስትራቴጅክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ እና በፕሬዝዳንቱ ድጋፍ ሰጪ ቡድን የተዘጋጁ የስራ ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል::

መድረኩ በተነሱት ቁልፍ ጉዳዮች ላይ የዘርፎችና የክፍሎች ቁመና የተለየበት እና ድጋፍ ለሚሹት የክትትል እና ጥሩ አፈፃፀም ላሳዩት ማበረታቻ የሚሆን የወደፊት አቅጣጫ አስቀምጦ ተጠናቋል::

በመጨረሻም ፕሬዚዳንቱ ለዩኒቨርሲቲው ህክምና ትምህርት ቤት/School of Medicine ለተማሪዎች ተግባራዊ የህክምና ትምህርት መስጫ እየተሰናዳ ያለውን ልዩ Cadaver Dissection Room ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ጎብኝተዋል::

#We_serve_the_community!

✍️ Public Relations Executive

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *