
ክክየምክር ቤት አባላቱ ለሴት ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ስልጠና እና የልምድ ልውውጥ ሰጡ::ክክ
#ሠመራዩኒቨርሲቲ_መጋቢት_27/2017 ዓ.ም_የአ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመራጭ ሴቶች ኮከስ ፣ ከሰው ሀብት ልማት ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከሠመራ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን ለዩኒቨርሲቲው ሴት ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ስልጠና እና የልምድ ልውውጥ መድረክ ተካሄዷል::

ስልጠናው በሕይወት ክህሎት ዙርያ ማለትም በGoal Setting, Time Management and Designing Your Future ላይ ያተኮረ ሲሆን ሴት የምክር ቤት አመራሮች የራሳቸውን የህይወት ተሞክሮአቸውን በዩኒቨርሲቲው ከመጀመሪያ ዓመት እስከ ተመራቂዎች ድረስ ከ 500 ለሚልቁ ሴት ተማሪዎች አካፍለዋል::
